ጋዜጠኞችና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀም

በዘመናዊው ዓለም የቴክኖሎጂ እድገት በሁሉም የሥራ መስኮች ላይ አሻራውን እያሳረፈ ይገኛል። ከነዚህም መካከል የጋዜጠኝነት ሙያ ዋነኛው ነው።

May 13, 2026 - 13:35
 0  2
ጋዜጠኞችና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀም

ጋዜጠኞችና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀም

​ግንቦት 5/2018 | አዲስ አበባ
​በዘመናዊው ዓለም የቴክኖሎጂ እድገት በሁሉም የሥራ መስኮች ላይ አሻራውን እያሳረፈ ይገኛል። ከነዚህም መካከል የጋዜጠኝነት ሙያ ዋነኛው ነው። ሆኖም ቴክኖሎጂው የሚያመጣቸውን ምቾቶች በንቃትና በኃላፊነት መጠቀም እንደሚገባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ዶ/ር አብዱላዚዝ ዲኖ አስገንዝበዋል።

​ዶ/ር አብዱላዚዝ እንደሚሉት፣ AI (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ጊዜን በመቆጠብ፣ የሥራ ቅልጥፍናን በማሻሻልና ጥራት ያለው ውጤት ለማውጣት ትልቅ አጋዥ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ረዳት ቴክኖሎጂ የሙያውን መሰረታዊ መርሆች ሊተካ እንደማይገባ ገልጸዋል።
​"ቴክኖሎጂው አማራጭ ሳይሆን የግድ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፤ ነገር ግን አጠቃቀሙ የሙያ ስነ-ምግባርን የጠበቀ መሆን አለበት።"

​ጋዜጠኞች ከAI የሚያገኟቸውን መረጃዎች ያለምንም ምርመራ በቀጥታ ለህዝብ ማቅረብ አደገኛ መሆኑን ምሁሩ ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው ስህተቶችን ሊሰራ ስለሚችል ​የመረጃ ምንጮችን ደጋግሞ ማረጋገጥ (Fact-checking)፣
​የመረጃውን ትክክለኛነት በሰውኛ እይታ መገምገም፣ ​ሚዛናዊነትን መጠበቅ ዋነኛው የቤት ስራ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

​ጋዜጠኞች በቴክኖሎጂው ከመጠን በላይ በመተማመን የማንበብ፣ የመመራመርና የፈጠራ (Creativity) ብቃታቸው እንዳይቀንስ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል። ከአለም ጋር እኩል ለመራመድ ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ ቢሆንም፣ የጋዜጠኛው የግል ብቃትና ጥልቅ እውቀት ግን ሁልጊዜም ቀዳሚው መሆን እንዳለበት ተገልጿል።

ቴክኖሎጂው በርካታ መልካም እድሎችን ይዞ የመጣ ቢሆንም፣ በተለይ በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ስነ-ምግባር "ለድርድር የማይቀርብ" ዋነኛ ምሰሶ መሆኑን ዶ/ር አብዱላዚዝ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow