በ55ኛው የኪነ-ጥበብ ምሽት ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ የክብር እንግዳ ሆኖ ይቀርባል

​መደበኛ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቱን ለታዳሚዎች ሲያቀርብ የቆየው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር እና ፊልም ጥበባት ትምህርት ክፍል የባህል ማዕከል የኪነ-ጥበብ ምሽት፣ 55ኛው መርሃ-ግብሩን በመጪው ረቡዕ ማለትም ዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያቀርብ ተገለጸ።

May 13, 2026 - 13:29
 0  2

​በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው የጥበብ ምሽት ላይ ታዋቂውና ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚገኝ ታውቋል። ድምፃዊው በመርሃ-ግብሩ ላይ በመገኘት በሙዚቃው ዘርፍ ያለውን የስኬት ጉዞና ያካበተውን ሰፊ ሙያዊ ልምድ ለታዳሚው እንደሚያካፍል ይጠበቃል።

​ዝግጅቱ ከልምድ ልውውጡ በተጨማሪ የተለያዩ ጥበባዊ ስራዎች የሚቀርቡበት ሲሆን፣ የኪነ-ጥበብ አፍቃሪዎች፣ ወጣት ባለሙያዎችና ተማሪዎች እንዲታደሙ ጥሪ ቀርቧል።
​የኪነ-ጥበብ ምሽት በተከታታይ በሚያዘጋጃቸው መርሃ-ግብሮች አንጋፋና ስመ-ጥሩ ባለሙያዎችን ከወጣቱ ትውልድ ጋር በማገናኘት የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ ምቹ መድረክ እየፈጠረ ይገኛል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow