ሳውዲ አረቢያን ያነጋገረው የድሮን ጥቃት ጥምር ኃይሉ ድሮኖችን በአየር ላይ መቶ አክሽፎዋቸዋል
በሳውዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ኃይል በመካ እና በምስራቃዊው የሀገሪቱ ክፍል ላይ ኢላማ ተደርገው የተተኮሱ ድሮኖችን በአየር ላይ በመጥለፍ ሙሉ በሙሉ ማውደሙ አረጋግጥዋል ።
ዓለም አቀፍ የዜና ማዕከላት እንደገለጹት፤ ጥምር ኃይሉ በወሰደው ፈጣን እና ኃይለኛ የጸጥታ እርምጃ በሀገሪቱ ቁልፍ አካባቢዎች ላይ ሊደርስ የነበረውን አደጋ አስቀድሞ መከላከል ተችሏል።
በተለይም በታላቁ እስላማዊ ቅዱስ ስፍራ አቅራቢያ የሚገኘው የመካ ክልል እና የምስራቃዊው የሳውዲ ክፍል የጥቃቱ ኢላማ ከነበሩት ስፍራዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
ይህ ድንገተኛ ክስተት በሳውዲ አረቢያ የአየር ክልል እና የጸጥታ ዙሪያ ትኩረትን የሳበ ሲሆን የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት እና ጥምር ኃይሉ የአየር ክልል ጥበቃውን በማጠናከር ማንኛውንም ያልተፈቀደ እና አደገኛ እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር በከፍተኛ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ተመላክቷል።
በድሮን ጥቃቱ ሳቢያ ስለደረሰ ጉዳት እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።
ሁቲዎች ከመስከረም ወር ጀምሮ የየመንን የባብ ኤል-ማንደብ ጠረፍ ስለሚቆጣጠሩ፣ ወደ ጂቡቲ፣ ፖርት ሱዳንና በርበራ የሚደረገው የቀይ ባሕር እንቅስቃሴ ለአደጋ እንደተጋለጠ ነው።
What's Your Reaction?