በ55ኛው የኪነ-ጥበብ ምሽት ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ የክብር እንግዳ ሆኖ ይቀርባል
መደበኛ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቱን ለታዳሚዎች ሲያቀርብ የቆየው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር እና ፊልም ጥበባት ትምህርት ክፍል የባህል ማዕከል የኪነ-ጥበብ ምሽት፣ 55ኛው መርሃ-ግብሩን በመጪው ረቡዕ ማለትም ዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያቀርብ ተገለጸ።

በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው የጥበብ ምሽት ላይ ታዋቂውና ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚገኝ ታውቋል። ድምፃዊው በመርሃ-ግብሩ ላይ በመገኘት በሙዚቃው ዘርፍ ያለውን የስኬት ጉዞና ያካበተውን ሰፊ ሙያዊ ልምድ ለታዳሚው እንደሚያካፍል ይጠበቃል።
ዝግጅቱ ከልምድ ልውውጡ በተጨማሪ የተለያዩ ጥበባዊ ስራዎች የሚቀርቡበት ሲሆን፣ የኪነ-ጥበብ አፍቃሪዎች፣ ወጣት ባለሙያዎችና ተማሪዎች እንዲታደሙ ጥሪ ቀርቧል።
የኪነ-ጥበብ ምሽት በተከታታይ በሚያዘጋጃቸው መርሃ-ግብሮች አንጋፋና ስመ-ጥሩ ባለሙያዎችን ከወጣቱ ትውልድ ጋር በማገናኘት የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ ምቹ መድረክ እየፈጠረ ይገኛል።
What's Your Reaction?