ብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ አወጣ!
ለሀገር ውስጥ አስመጪዎችና ላኪዎች ትልቅ እፎይታ ይሆናል የተባለለት አዲስ ሀግ ብሄራዊ ባንክ አወጣ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) የውጭ ምንዛሬ አስተዳደርን ይበልጥ ለማቀላጠፍ አዲስ መመሪያ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ። ለሀገር ውስጥ አስመጪዎችና ላኪዎች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል በተባለለት ዚህ አዲሱ አሰራር መሠረት የውጭ ምንዛሬ አካውንት እና የሪቴንሽን አካውንት ያላቸው ተቋማት፣
ከዚህ ቀደም ከማዕከላዊ ባንክ ማግኘት ይገባቸው የነበረውን ቅድመ-ፈቃድ ሳይጠብቁ በንግድ ባንኮች በኩል በቀጥታ የብድር ሰነድ (LC) እና CAD ማጽደቅ እንዲችሉ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። ውሳኔው አስመጪዎች የሚያጋጥሟቸውን ቢሮክራሲያዊ መዘግየቶች ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ሲሆን፣ ከኤልሲ (LC) ጋር ተያይዘው የሚጠየቁ የአገልግሎት ክፍያዎችንም ከዓለም አቀፍ አሰራር ጋር ለማጣጣም በየዓመቱ ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ እንዲቀነሱ ታዟል። ይህም የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በእጅጉ ያነቃቃል ተብሏል።ይህ ቤሮክራሲውን ያስቀራል ክፍያዎችን ያስተካክላ የተባለለት አዲሱ አሰራር መቼ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን አልተገልፀም
What's Your Reaction?