የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ለተመራቂዎችና ለሥራ ፈላጊዎች እያካሄደ ያለውን የምርምር እና የሥራ መድረክ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ አስተዳደር ከተሸጋገረ በኋላ ያዘጋጀውን የምርምር፣ የፈጠራ እና የሥራ አውደ-ርዕይ ሳምንት ዛሬ በይፋ ጀምሯል። ለተከታታይ ሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ የተማሪዎች የፈጠራ ሥራዎችና የምርምር ውጤቶች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን፣ ተመራቂዎችንና የሥራ ፈላጊዎችን ከቀጣሪ ተቋማት ጋር ለማገናኘት ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል

May 6, 2026 - 17:50
 0  2
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ለተመራቂዎችና ለሥራ ፈላጊዎች እያካሄደ ያለውን የምርምር እና የሥራ መድረክ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ለተመራቂዎችና ለሥራ ፈላጊዎች እያካሄደ ያለውን የምርምር እና የሥራ መድረክ  

አዲስ አበባየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ  አስተዳደር ከተሸጋገረ በኋላ ያዘጋጀውን የምርምር፣ የፈጠራ እና የሥራ አውደ-ርዕይ ሳምንት ዛሬ በይፋ ጀምሯል። ለተከታታይ ሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ የተማሪዎች የፈጠራ ሥራዎችና የምርምር ውጤቶች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን፣ ተመራቂዎችንና የሥራ ፈላጊዎችን ከቀጣሪ ተቋማት ጋር ለማገናኘት ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል።

ይህ መድረክ በተለይ ዘንድሮ ለሚመረቁ ተማሪዎች እና ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ወሳኝ የዕድል ድልድይ ከመሆኑም ባሻገር ዪንቨርስቲው  ከትምህርት አሰጣጥ ባለፈ ለአገራዊ ልማትና ለወጣቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ያለውን ትልቅ ኃላፊነት መወጣት መጀመሩን ያሳያል። የምርምር እና የሥራ መድረክ ዋነኛው ግቡም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያካበቱትን ዕውቀትና የፈጠራ ሥራዎችን በቀጥታ ከኢንዱስትሪው ፍላጎት ጋር ማስተሳሰር ነው።

·       የቀጥታ ትስስር፦ ተማሪዎች የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ለቀጣሪዎችና ለኢንቨስተሮች በተግባር በማሳየት የሥራ ዕድል የሚያገኙበት ሰፊ በር ተከፍቷል።

·       የገበያ ፍላጎትን መረዳት፦ ተመራቂዎች የአሰሪዎችን ፍላጎት በቅርበት እንዲረዱ እና ራሳቸውን ለገበያው ብቁ አድርገው እንዲያዘጋጁ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን አስመርቆ ከመሸኘት ባለፈ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ከተግባራዊ ምርምር ጋር በማስተሳሰር ግንባር ቀደም አገራዊ ኃላፊነቱን ከመወታቱም ባሻገር ተማሪዎች የፈጠራ ባለቤትና የሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በማስቻል፣ የአገሪቱን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ለመሙላትና የኢኮኖሚ መዋቅሩን በዕውቀት ለመደገፍ ዩኒቨርሲቲው የያዘውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበት ነው።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow