ከበባ የሚመስል ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ እየከፈተችብን ነው

ግብፅ በቀጠናው 'ከበባ' የሚመስል ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ እየከፈተችብን ነው!"የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

May 22, 2026 - 13:43
 0  2
ከበባ የሚመስል ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ እየከፈተችብን ነው

ግብፅ በቀጠናው 'ከበባ' የሚመስል ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ እየከፈተችብን ነው!"የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

የአፍሪካ ቀንድ የጂኦፖለቲካ ሙቀት ጣሪያ እየነካ ይመስላል የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጠንከር ያለ መግለጫ፣ ካይሮ በኢትዮጵያ ላይ “ቀጥተኛ የከበባ ስትራቴጂ”  በመዘርጋት ቀጠናውን ወደ ከፋ ውጥረት እየገፋችው መሆኑን በይፋ አጋልጥዋል።

ግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብን (GERD) ግንባታ ለማስተጓጎል እና ኢትዮጵያ በቅርቡ ያገኘችውን የታሪካዊ የባህር በር አማራጭ ለማክሸፍ፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጦር መተማመኛ እና የባህር ሃይል ስምምነቶችን በከፍተኛ ፍጥነት እያካሄደች ትገኛለች።ሚኒስቴሩ የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት እና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ማናቸውንም "የቀይ ባህር እና የአፍሪካ ቀንድ የሃይል ሚዛን ማዛባት" በትኩረት እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል። አክሎም፣ ኢትዮጵያ ይህንን ከበባ ለመስበር ሁሉንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ እና ስትራቴጂያዊ ግብረ-መልሶች ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን አስገንዝቧል።

ይህ የግብፅ እንቅስቃሴ በቀጠናው ያሉትን ታሪካዊ ባላንጣዎች ወደ ቀጥተኛ ፍጥጫ እያስገባቸው ሲሆን፣ የዓለም አቀፉን የንግድ መስመር ባብ-ኤል-ማንደብ የደህንነት ስጋት ውስጥ ጥሎታል ብለዋል .

ሎሚ ዜና ከፕሮፓጋንዳ ጀርባ ያሉትን እውነተኛ የፖለቲካ-ኢኮኖሚ እና የጂኦፖለቲካ ምስጢሮች ቀድመው ይረዱ!

ፈጣን እና ትንታኔያዊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow