የምዕራባውያንን የፋይናንስ የበላይነት ለመስበር የተገነባው "CBE Connect" ሥራ ጀመረ

ኢትዮጵያ በውጭ ፖለቲካዊ ተጽዕኖዎች የሚመጣን የኢኮኖሚ ጫና ለመመከት እና የምዕራባውያንን የፋይናንስ ሥርዓት (SWIFT) የበላይነት ለመስበር የሚያስችል፣ በራሷ ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚውል ዲጂታል የውጭ ምንዛሬ መላኪያ መረብ በይፋ ሥራ አስጀምራለች።

Jun 10, 2026 - 10:30
 0  6
የምዕራባውያንን የፋይናንስ የበላይነት ለመስበር የተገነባው "CBE Connect" ሥራ ጀመረ

ኢትዮጵያ በውጭ ፖለቲካዊ ተጽዕኖዎች የሚመጣን የኢኮኖሚ ጫና ለመመከት እና የምዕራባውያንን የፋይናንስ ሥርዓት (SWIFT) የበላይነት ለመስበር የሚያስችል፣ በራሷ ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚውል ዲጂታል የውጭ ምንዛሬ መላኪያ መረብ በይፋ ሥራ አስጀምራለች።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀገር በቀሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ኢግል ላዮን ጋር በመተባበር የገነባው ይህ "CBE Connect Digital Wallet"፣ በየዓመቱ በጥቁር ገበያ (ሃዋላ) የሚባክነውን ከ35 ቢሊዮን ዶላር በላይ የዲያስፖራ ገንዘብ ወደ ሕጋዊ መስመር ለማስገባት ያለመ ነው። በአሁኑ ወቅት በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገር እየገባ ያለው የውጭ ምንዛሬ 22 በመቶ (7.2 ቢሊዮን ዶላር) ብቻ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

የኢግል ላዮን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በሱፈቃድ ጌታቸው "ይህ መተግበሪያ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ የፋይናንስ መሠረተ-ልማት ነው፤ የውጭ ፖለቲካ ኃይሎች የገንዘብ ፍሰታችንን ሊዘጉብን የማይችሉበትን አቅም ፈጥረናል" ብለዋል።
በብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ለውጥ መሠረት ፕላትፎርሙ ግለሰቦች የውጭ ምንዛሬን (ዶላር/ዩሮ) በዲጂታል መንገድ (Dollar Wallet) እንዲይዙ የፈቀደ ሲሆን፣ ይህም ከዚህ ቀደም የተከለከለ ነበር።

ሥርዓቱ በሳውዲ አረቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዩኤሬ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቀላሉ ገንዘብ ልከው ለ70 ሚሊዮን የባንክ ሂሳቦች በቅጽበት ተደራሽ እንዲያደርጉ ያስችላል። ይህም ኢትዮጵያ ከምዕራባውያን ጥገኝነት ለመላቀቅ የምታደርገው ስትራቴጂካዊ አካሄድ ተደርጎ ተወስዷል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow