የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ እያዘመነ መሆኑን አስታወቀ
የአገሪቱ ቀዳሚ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎቱን ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ለማስኬድ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።
የአገሪቱ ቀዳሚ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎቱን ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ለማስኬድ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።
ዩኒቨርሲቲው የጀመረው ይህ የማዘመን ሥራ የተጠቃሚዎቹን ፍላጎት በብቃት ለማሟላትና የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና ምቹ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አብያተ-መጻሕፍት ዋና ኃላፊ ዶክተር ለማ ለሳ እንደገለጹት፤ የተጀመረው የሪፎርም ሥራ በተለይም የመጽሐፍትና የምርምር ሥራዎችን በዲጂታል መልክ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በዚህም መሠረት ተማሪዎችና ተመራማሪዎች በግቢው ውስጥ በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው፣ ባሉበት ቦታ ሆነው በኢንተርኔት አማካኝነት የተለያዩ ኢ-መጽሐፍትን (E-books) እና ዓለም አቀፍ የሳይንስ መጽሔቶችን (Journals) በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት የዲጂታል ሥርዓት ተዘርግቷል።
ቤተ-መጻሕፍቱ አገልግሎቱን ከማዘመን ጎን ለጎን የሚከተሉትን ግብዓቶች በኤሌክትሮኒክ መልክ አዘጋጅቶ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ለሌሎች ተመራማሪዎች ክፍት ማድረጉን ኃላፊው ጠቁመዋል።
ዶክተር ለማ አያይዘውም፣ ቤተ-መጻሕፍቱ ዘመኑን የዋጁ የቴክኖሎጂ ለውጦችን እያካሄደ ቢገኝም፣ ከተጠቃሚዎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ግን አሁንም ክፍተቶች መኖራቸውን አልሸሸጉም። ተማሪዎችና ተመራማሪዎች የተዘጋጁትን እነዚህን ሰፊ የዲጂታል ግብዓቶች በአግባቡና በልዩ ትኩረት ሊጠቀሙባቸው እንደሚገባም ኃላፊው አሳስበዋል።
What's Your Reaction?