የኢትዮጵያየብድር ሽግሽግ ድርድር እና የፋይናንስ ሚኒስቴር ይፋዊ መግለጫ

 የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የቦንድ አበዳሪዎች ጋር የተደረገው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ሽግሽግ ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ተገለጠ

May 29, 2026 - 19:17
 0  2
የኢትዮጵያየብድር ሽግሽግ ድርድር እና የፋይናንስ ሚኒስቴር ይፋዊ መግለጫ

 የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የቦንድ ባለቤቶች (Eurobond Holders) ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንታት (ከግንቦት 6 እስከ ግንቦት 27 ቀን) ሲያካሂድ የነበረው 1 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ሽግሽግ (Debt Restructuring) ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁን በይፋ አስታወቀ።

መንግስት ባለፈው ጥር ወር ላይ ከአበዳሪዎች ጋርበመርህ ደረጃላይ ደርሶበት የነበረው ስምምነት፣ በፓሪስ ክለብ እና በባለብዙ ወገን አበዳሪዎች ስብስብ (Official Creditor Committee - OCC) ውድቅ መደረጉ ይታወሳል። የኦሲሲ (OCC) ኮሚቴ ስምምነቱን ውድቅ ያደረገውሁሉንም አበዳሪዎች በእኩልነት የማስተናገድ” (Comparability of Treatment) መርህን አይከተልም በሚል ነበር።

 መንግስት የኦሲሲን አስተያየት መነሻ በማድረግ የሀገሪቱን የወደፊት የኢኮኖሚ እድገት ታሳቢ ያላደረገ አዲስ የተሻሻለ ረቂቅ ቢያቀርብም፣ የቦንድ አበዳሪዎቹ ኮሚቴ (Ad Hoc Committee) ሀሳቡን በሙሉ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል። የፋይናንስ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ የሀገሪቱን የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ጥንካሬ ለመጠበቅ እና ቡድን 20 ሀገራት መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ፍትሃዊ እና ግልፅ ድርድርን በቅን ልቦና ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow