የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ጸደቀ ለኢንቨስትመንት አዲስ በር፣ ለኮንትሮባንድ ጠንካራ ምላሽ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
በአዋጅ ቁጥር 1425/2018 ሆኖ የጸደቀው ይህ አዲስ ሕግ፣ የኮንትሮባንድ ንግድን በቁርጠኝነት ለመከላከልና በጉምሩክ አሠራር ውስጥ ፍትሐዊነትን ለማስፈን ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ማሻሻያው የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ያገናዘበ፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉንና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ እንዲሁም አስመጪዎች በቀረጥና ታክስ አወሳሰን ላይ የሚያቀርቧቸውን አቤቱታዎች የሚያቀልል መሆኑ ተመላክቷል።
በሌላ በኩል፣ በኮንትሮባንድ ጭነት ምክንያት ተሽከርካሪዎችን ከመውረስ ጋር ተያይዞ በነበረው አሠራር ላይ አዲስ ማስተካከያ ተደርጓል። ንብረቱ የተያዘበት ባለቤት በድርጊቱ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ የሌለው መሆኑ ከተረጋገጠ ንብረቱ ሊወረስ እንደማይገባ በአዋጁ ተደንግጓል።
ሆኖም ባለቤቶች ተሽከርካሪዎቻቸውን ለአሽከርካሪዎች በውል ሲያስረክቡ ሕግ አክባሪ ሹፌሮችን የመቅጠርና ለሚፈጠሩ ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ተገቢውን ዋስትና የመውሰድ ኃላፊነት እንዳለባቸው በጥብቅ ተገልጿል።
What's Your Reaction?