ኢትዮጵያና አሜሪካ ስልታዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በዋሽንግተን ዲሲ ምክክር አደረጉ።

ኢትዮጵያና አሜሪካ ያላቸውን ታሪካዊና የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ ስልታዊ የምክክር መድረክ በዋሽንግተን ዲሲ አካሂደዋል።

May 12, 2026 - 10:57
 0  2
ኢትዮጵያና አሜሪካ ስልታዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በዋሽንግተን ዲሲ ምክክር አደረጉ።

ኢትዮጵያና አሜሪካ ስልታዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በዋሽንግተን ዲሲ ምክክር አደረጉ።

​ኢትዮጵያና አሜሪካ ያላቸውን ታሪካዊና የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ ስልታዊ የምክክር መድረክ በዋሽንግተን ዲሲ አካሂደዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዴዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተመራውና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ከአሜሪካ አቻዎቹ ጋር በጋራ ጥቅሞችና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት መክሯል።​ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረገው ከፍተኛ የምክክር መድረክ በሦስት ቁልፍ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ እነሱም፦

# ​ኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት፦ የንግድ ትስስርን ማሳለጥና የኢኮኖሚ ብልጽግናን ማረጋገጥ

# ​መከላከያና ደህንነት፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጸጥታ ትብብር ማጠናከር

# ​ቀጠናዊ ሰላም፦ በምስራቅ አፍሪካ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በጋራ መስራት የሚሉ ናቸው።

​በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩን እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ያካተተ ሲሆን፣ መድረኩ የሁለቱን ሀገራት ስልታዊ ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል። ይህ አዲስ የምክክር ማዕቀፍ የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ይበልጥ ዘላቂና ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያግዝም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow