'የፋርስ አንበሶች ወደ ዓለም መድረክ 'የኢንፋንቲኖ ቁርጠኝነት! "ፖለቲካው ቢነጥለንም፣ እግር ኳሱ ግን አንድ ያደርገናል!" — ጃኒ ኢንፋንቲኖ
የፋርስ አንበሶች ወደ ዓለም መድረክ — የኢንፋንቲኖ ቁርጠኝነት! በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ምክንያት ተሳትፎዋ አጠራጣሪ ሆኖ የነበረው የኢራን ብሔራዊ ቡድን፣ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ መገኘቱ በይፋ ተረጋግጧል። የፊፋ ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ "እግር ኳስ ድልድይ ነው" በማለት ለቡድኑ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
"ፖለቲካው ቢነጥለንም፣ እግር ኳሱ ግን አንድ ያደርገናል!" — ጃኒ ኢንፋንቲኖ
በአለም አቀፍ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ተሳትፎዋ ትልቅ ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የነበረው የኢራን ብሔራዊ ቡድን፣ በመጨረሻ ወደ 2026ቱ የዓለም ዋንጫ የሚያደርገው ጉዞ በይፋ መረጋገጡን የፊፋ ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ አስታውቀዋል
ከውዝግብ ጀርባ ያለ ድል
ላለፉት ወራት የኢራን ብሄራዊ እግርኩዋስ ቡድን በዓለም ዋንጫ ላይ መገኘት በበርካታ ዝርዝር ዲፕሎማሲያዊ ምክንያቶች ሲያወዛግብ ቆይቷል። ብዙዎች "ኢራን ከውድድሩ ልትታገዳ ትችላለች" የሚል ስጋት ቢያድራቸውም፣ የፊፋው ፕሬዝዳንት ግን ለቡድኑ ያላቸውን ጥልቅ ክብር እና መልካም ምኞት በመግለጽ፣ ስፖርት ከፖለቲካ በላይ መሆኑን ለዓለም አስመስክረዋል።
ወደ ዙሪክ የሚያመራው ጥሪ!
ይህ የምስራች ይበልጥ እውን የሚሆነው በመጪው ግንቦት 12 ቀን ወደ የ ፊፋን ጥሪ አክብሮ ዙሪክ የሚያመራው የ ኢራን ብሄራዊ ቡድን ይፋ ሲሆን ነው ። የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዙሪክ በሚገኘው የፊፋ ዋና መሥሪያ ቤት ለሚደረገው ወሳኝ የዝግጅት ስብሰባ በክብር ተጋብዟል። ይህ ስብሰባ የኢራን "የፋርስ አንበሶች" በሰሜን አሜሪካ ምድር ለሚያደርጉት ታሪካዊ ተሳትፎ የመጨረሻውን መስመር የሚነድፍ ይሆናል። ቀጣዩ ምዕራፍግንቦት 12 ቀን 2018 በዙሪክ በሚገኘው የፊፋ ዋና መሥሪያ ቤት የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዝግጅት ስብሰባ ይጠበቃል።
የኢንፋንቲኖ ማረጋገጫ ለኢራን ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን፣ እግር ኳስን ለሚወዱ ሁሉ ትልቅ የምስራች ነው። አሁን ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሜዳው ተመልሷል፤ የፋርስ አንበሶች በዓለም መድረክ ምን አስደናቂ ታሪክ ይዘው ይመጡ ይሆን? ሎሚ ዜና የዓለም ዋንጫው ትኩስ መረጃዎች ባሉበት ይደርሱዎታል!
- የሞሮኮ ዝግጅት፦ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ልምምድ የሚያደርግበትን ዋና ማዕከል በኒው ጀርሲ (New Jersey) ለማድረግ መምረጡ ታውቋል።
- የትኬት ዋጋ ውዝግብ፦ የዓለም ዋንጫ ትኬት ዋጋ እጅግ በጣም ውድ መሆን የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። አንዳንድ ለቤተሰብ የታሰቡ ትኬቶች እስከ 3,000 ዶላር የደረሱ ሲሆን፣ ለፍፃሜው ጨዋታ የቀረቡ ምርጥ መቀመጫዎች እስከ 33,000 ዶላር እየተጠየቀባቸው መሆኑ አድናቂዎችን አስቆጥቷል። ፊፋ ይህንን ዋጋ በአሜሪካ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት ጋር አያይዞታል።
- የ48 ቡድኖች ዝርዝር፦ ለመጀመሪያ ጊዜ 48 አገራት የሚሳተፉበት ይህ የዓለም ዋንጫ፣ ሁሉንም ተሳታፊ አገራት አረጋግጧል። ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኢራቅ የመጨረሻዎቹን ቦታዎች ይዘዋል።
- የኢትዮጵያ ሁኔታ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ከዚህ ቀደም በነበሩ የማጣሪያ ጨዋታዎች በደረሰባቸው ሽንፈት ምክንያት ለ2026 ዓለም ዋንጫ የማለፍ ዕድላቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።
የአለም ዋንጭ እና የተጫዋቾች ጉዳት፦
ኒይማር (ብራዚል)፦ አሁንም ድረስ ሙሉ ብቃቱ ላይ ባለመሆኑ ለብራዚል ስብስብ መካተቱ አጠራጣሪ ሆኗል።
ሎሚ ዜና — የዓለም ዋንጫው ትኩስ መረጃዎች ባሉበት ይደርሱዎታል!
What's Your Reaction?