የ14.1 ቢሊዮን ዶላር የኢነርጂ አብዮት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል መሪነቷን የምታረጋግጥበትንና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚቀይር ግዙፍ የኃይል ፕሮጀክት ይፋ አደረገች። በ4ኛው “Invest in Ethiopia” ፎረም ላይ ቃሉ የተገባውና በቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ሚንግ ያንግ ግሩፕ (Ming Yang Group) የሚተገበረው የ14.1 ቢሊዮን ዶላር የኢነርጂ አብዮት የኢንቨስትመንት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ስራ ገብቷል

May 11, 2026 - 19:34
 0  4
የ14.1 ቢሊዮን ዶላር የኢነርጂ አብዮት በኢትዮጵያ

14.1 ቢሊዮን ዶላር! ታሪካዊው "የኢነርጂ አብዮት" በይፋ ተጀመረ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል መሪነቷን የምታረጋግጥበትንና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚቀይር ግዙፍ የኃይል ፕሮጀክት ይፋ አደረገች። 4ኛው “Invest in Ethiopia” ፎረም ላይ ቃሉ የተገባውና በቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ሚንግ ያንግ ግሩፕ (Ming Yang Group) የሚተገበረው 14.1 ቢሊዮን ዶላር የኢነርጂ አብዮት የኢንቨስትመንት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ስራ ገብቷል።ይህ ፕሮጀክት የተለመደው አይነት  የኃይል ማመንጫ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የታዳሽ ኃይል ካርታ ላይ ከፊት የሚያስቀምጥ ነው። ጠቅላላ የኃይል መጠን፦ 8.4 ጊጋ ዋት (ከንፋስ እና ከፀሐይ)

  • ጠቅላላ የኢንቨስትመንት ፈሰስ፦ 14.1 ቢሊዮን ዶላር በነገራችን ላይ ይህ  የ 14 ቢልየን የገንዘብ መጠን ከመጀመሪያው እቅድ 4.1 ቢሊዮን ዶላር በማደግ ክብረ ወሰን የሰበረ ሲሆን ደቡብ ኦሞ፣ አፋር እና ሶማሌ በዚህ የአኢነርጂ አብዪት ተጥቃሚ የሚሆኑ  ክልሎችናቸው ተብልዋል

ታሪካዊው "የኢነርጂ አብዮ ምዕራፍ አንድ የኃይል መረቡን ማጠናከር ሲሆን 7.47 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይፈጃል በመጀመሪያው ምዕራፍ 5.4 ጊጋ ዋት ከንፋስ እና 2.8 ጊጋ ዋት ከፀሐይ ብርሃን በማመንጨት የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ እና የቤት ውስጥ የኃይል ፍላጎት እንደሚያሙዋላ ተነግሮዋል

በቀጣይ ምዕራፍ ሁለየቴክኖሎጂ ሽግግር እና የኢንዱስትሪ ማዕከል 7.3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር

ከኃይል ማመንጨት ባለፈ ኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አምራች ያደርጋታል። በሁለተኛው ምዕራፍ የሚከተሉት ግዙፍ ፋብሪካዎች ይገነባሉ፦

  • አረንጓዴ አሞንያ (Green Ammonia) ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርብ ንጹህ ነዳጅ።
  • የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መሳሪያዎች ማምረቻ፦ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን የሚሸፍን ፋብሪካ።
  • የንፋስ ኃይል ማመንጫ መገልገያዎች (Wind Turbine) ፋብሪካ፦ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የንፋስ ኃይል መለዋወጫ ማዕከል የሚያደርግ ነው

ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን የኃይል አቅርቦት ወደ ላቀ ደረጃ ከማሸጋገሩ ባለፈ፣ ሀገሪቱ ለታላላቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተመራጭ መዳረሻ መሆኗን ያረጋገጠ ነው። ፕሮጀክቱ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ በክልሎች መካከል የሚታየውን የኢኮኖሚ ትስስር ያጠናክራል።

 ለተጨማሪ መረጃዎች ድህረ ገጻችንን [lomiinews.com] ይጎብኙ።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow