የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ሚና ለካፒታል ገበያና ለዲጂታል ንግድ ሽግግር
የብሉምበርግ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ አፍሪካ (BMIA) ከአዲስ አበባ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ከሚዲያ፣ ፋይናንስ፣ ኮሙኒኬሽንና ቴሌኮም ዘርፎች የተውጣጡና 30 በመቶ ያህሉ ሴቶች የሆኑባቸውን 101 የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ባለሙያዎችን አስመርቋል።
የብሉምበርግ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ አፍሪካ (BMIA) ከአዲስ አበባ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ከሚዲያ፣ ፋይናንስ፣ ኮሙኒኬሽንና ቴሌኮም ዘርፎች የተውጣጡና 30 በመቶ ያህሉ ሴቶች የሆኑባቸውን 101 የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ባለሙያዎችን አስመርቋል።
በምረቃው ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ስልጠናው በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ፣ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን ለዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትና ለዴሞክራሲ ስርዓት መሰረት የሚሆን መሆኑን ገልጸው፣ ተመራቂዎች ውስብስብ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን ለህዝብና ለፖሊሲ አውጪዎች በግልጽ ተርጉመው ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በሌላ በኩል የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ከፖለቲካ በተለየ መልኩ ጥንቃቄ የሚፈልግና ሙሉ በሙሉ በቁጥርና በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት በአብነት አስገንዝበዋል። ሀገሪቱ ወደ ካፒታል ገበያና ዲጂታል ንግድ በገባችበት በዚህ ወቅት መረጃ ለባለሀብቶች ወሳኝ መተማመኛ በመሆኑ ባለሙያዎቹ እውቀታቸውን በሃላፊነትና በድፍረት እንዲጠቀሙበት የጠቆሙት ፕሬዜዳንቶቹ፣ ተመራቂዎቹ የዘመኑን የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ ለፋይናንስ ዘገባ ጥራት ማሻሻያ እንዲጠቀሙበትም መክረዋል።
What's Your Reaction?