ጎግል የደረሰበት የቴክኖሎጂ እድገት እና ላብራቶሪ ውስጥ ያደጉ የወባ ትንኞች
የቴክኖሎጂው ግዙፍ ኩባንያ ጎግል በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን ለመቀነስ 32 ሚሊዮን በላብራቶሪ ውስጥ ያደጉ ተባዕት ጾታ ትንኞችን በፍሎሪዳና በካሊፎርኒያ ግዛቶች ውስጥ ለመልቀቅ ፍቃድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
የቴክኖሎጂው ግዙፍ ኩባንያ ጎግል በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን ለመቀነስ 32 ሚሊዮን በላብራቶሪ ውስጥ ያደጉ ተባዕት ጾታ ትንኞችን በፍሎሪዳና በካሊፎርኒያ ግዛቶች ውስጥ ለመልቀቅ ፍቃድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ. በ2014 የተጀመረውና በሽታ አምጪ የትንኝ ዝርያዎችን ለመቆጣጠር አዳዲስ መንገዶችን የሚያጠናው የጎግል "ዲበግ" የተባለ ተነሳሽነት አካል ነው። ኩባንያው በየዓመቱ 16 ሚሊዮን ትንኞችን ለመልቀቅ ያቀደ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት ፕሮፖዛሉ በአሜሪካ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ እየተገመገመ ይገኛል።
እነዚህ ወንድ ትንኞች "ዎልባቺያ" በተባለ የባክቴሪያ ዝርያ የተበከሉ በመሆናቸው፥ ከተፈጥሮአዊ ሴት ትንኞች ጋር በሚጣመሩበት ጊዜ እንቁላሎቹ ሳይፈልቁ እንዲቀሩ ያደርጋሉ፤ ይህም የትንኞችን ቁጥር በሂደት በእጅጉ ይቀንሰዋል። በላብራቶሪ የተዘጋጁት ወንድ ትንኞች ብቻ ሲሆኑ፥ ወንድ ትንኞች ደግሞ ሰውን ፈጽሞ እንደማይነክሱ ታውቋል። ይህ አዲስ የሳይንስ አካሄድ ስኬታማ ከሆነ በትንኞች አማካኝነት የሚመጡ ገዳይ በሽታዎችን ለመከላከል ትልቅ እፎይታን ይዞ ይመጣል ተብሎ ይገመታል።
What's Your Reaction?