ፈረንሳይና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርትና ባህል ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት ይበልጥ አጠናከሩ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ መልኩ የታደሰውን የተማሪዎች መማሪያና መዝናኛ ስፍራ በይፋ ተመርቋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ መልኩ የታደሰውን የተማሪዎች መማሪያና መዝናኛ ስፍራ በይፋ መርቋል።
ከምረቃው ጎን ለጎንም የካምፓስ ፍራንስ ኢትዮጵያ (Campus France Ethiopie) እና የአሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴዝ (Alliance Ethio-française) እንቅስቃሴዎችንና አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ካምፓሱ የሚያመጣ አዲስ የትብብር አጋርነት ይፋ ሆኗል።
ይህ አጋርነት ተማሪዎች በፈረንሳይ ሀገር የሚገኙ የትምህርት ዕድሎችን፣ ዓለም አቀፍ የተማሪዎች ዝውውርን እና የፍራንኮፎኒ (የፈረንሳይኛ ቋንቋና ባህል) ማህበረሰብን በቀላሉ እንዲቀላቀሉ ትልቅ በር የሚከፍት ነው ተብሏል።
ለዚህ ስኬት መሳካትና ለአጋርነቱ መመስረት ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና ለአለም አቀፍ የፍራንኮፎኒ ድርጅት (OIF) ተወካይ ክብርት ኔፈርቲቲ ሙሺያ ሺባንዳ ለነበራቸው ተሳትፎና ላበረከቱት አስተዋፅኦ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ የላቀ ምስጋና አቅርቧል።
What's Your Reaction?