ፓስፖርት ለመውሰድ ወረፋና እንግልት ሊያበቃ ነው! — አዲሱ የኢሚግሬሽን የዲጂታል ጉዞ
ፓስፖርት ለማውጣት ወይም ለማደስ ቀጠሮ መያዝ፣ ማለዳ ተነስቶ በተቋሙ ደጅ መሰለፍ እና አሻራዎን ለመስጠት መኳተን ታሪክ ሊሆን ነው።
ፓስፖርት ለማውጣት ወይም ለማደስ ቀጠሮ መያዝ፣ ማለዳ ተነስቶ በተቋሙ ደጅ መሰለፍ እና አሻራዎን ለመስጠት መኳተን ታሪክ ሊሆን ነው። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተገልጋዮችን ሕይወት በእጅጉ የሚያቃልል ፍጹም ዲጂታል የሆነ አሠራር ይዞ ብቅ ማለቱን አብስሯል።
አሻራ ለመስጠት በአካል መገኘት ይቀራል፡ ከአሁን በኋላ «ለአሻራ በአካል ተገኙ» የሚለው አድካሚ ሒደት ይቆማል።
የፋይዳ መታወቂያዎ ፓስፖርትዎ ነው፡ የፓስፖርት ሲስተሙ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር እየተቀናጀ በመሆኑ፣ ሲስተሙ የእርስዎን መረጃ በቀጥታ ከፋይዳ ቋት ላይ ይወስዳል። እርስዎ የሚጠበቅብዎት ከቤትዎ ሳይወጡ በኢንተርኔት ማመልከት ብቻ ነው።
ለደላሎችና ለአጭበርባሪዎች በኦንላይን ምዝገባ ስም ዜጎችን የሚያታልሉ አካላትን ለመግታት ተቋሙ ጥብቅ የቴክኖሎጂ አጥር አጥሯል። አንድ ሰው ከአንድ ቦታ ሆኖ ከ10 በላይ ሰዎችን መመዝገብ የማይችልበት አዲስ የቁጥጥር ሥርዓት ተዘርግቷል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት እንዳረጋገጡት ይህ አሠራር ሙሉ በሙሉ ሲተገበር የፓስፖርት አገልግሎት ፍጹም ዘመናዊ፣ ፈጣንና ከእንግልት የጸዳ ይሆናል። ቴክኖሎጂ የኢሚግሬሽንን በር እያንኳኳ ነው። ከቤት ሳይወጡ ፓስፖርት በእጅዎ የሚገባበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም!
What's Your Reaction?