ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የስራ መልቀቂያ አቀረቡ
በኢራን ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጥልቅ የመዋቅር እና የውሳኔ አሰጣጥ ክፍፍል መፈጠሩን የሚያሳይ አዲስ ክስተት ተሰማ። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ለሀገሪቱ የበላይ መሪ ጽህፈት ቤት ይፋዊ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ምንጭ ለኢራን ኢንተርናሽናል ገልጿል።
በኢራን ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጥልቅ የመዋቅር እና የውሳኔ አሰጣጥ ክፍፍል መፈጠሩን የሚያሳይ አዲስ ክስተት ተሰማ። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ለሀገሪቱ የበላይ መሪ ጽህፈት ቤት ይፋዊ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ምንጭ ለኢራን ኢንተርናሽናል ገልጿል።
ፕሬዝዳንቱ እሁድ ዕለት ባስገቡት በዚህ ደብዳቤ ላይ፤ እሳቸውና መንግስታቸው በሀገሪቱ ዋና ዋና እና ወሳኝ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ መገለላቸውን አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።
በፕሬዚዳንቱ መገለል ምክንያት በተፈጠረው ሰፊ ክፍተት፤ በኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር (IRGC) ውስጥ ያሉ ጽንፈኞች የሀገሪቱን ቁልፍ ጉዳዮች እና መሪነቱን በቀጥታ እንዲቆጣጠሩ ዕድል እንደሰጣቸው ምንጩ ጠቁሟል።
ካጋጠማቸው የቁጥጥር መጥፋት እና ጫና የተነሳ በአስቸኳይ ከስልጣናቸው ለመልቀቅ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል።
የወደፊት ዕጣ ፈንታ እና የበላይ መሪው ውሳኔ
ይህ የደብዳቤ ይዘት በኢራን ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ታይቶ የማይታወቅና ጥልቅ የሆነ የስልጣን ክፍፍል መኖሩን በግልጽ ያሳያል።
የሀገሪቱ የበላይ መሪ የሆኑት ሞጅታባ ኻሜኒ የፕሬዝዳንቱን የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ይቀበሉት ወይም ውድቅ ያድርጉት እስካሁን በይፋ የታወቀ ነገር የለም። ሆኖም ግን ይህ እርምጃ የኢራንን የውስጥ ፖለቲካዊ መረጋጋት ይበልጥ ወደ ከፋ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ።
What's Your Reaction?