18ተኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የመጻሕፍት አውደ-ርዕይ በይፋ ተከፈተ
በምርምር የተደገፉ መጻሕፍትን በማሳተምና በማከፋፈል በትውልድ መካከል የእውቀት ትስስር መፍጠር እንደሚገባ ተጠቆመ። ይህ የተገለጸው ከሰኔ 1 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው 18ተኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የመጻሕፍት አውደ-ርዕይ በይፋ በተከፈተበት ወቅት ነው።
በምርምር የተደገፉ መጻሕፍትን በማሳተምና በማከፋፈል በትውልድ መካከል የእውቀት ትስስር መፍጠር እንደሚገባ ተጠቆመ። ይህ የተገለጸው ከሰኔ 1 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው 18ተኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የመጻሕፍት አውደ-ርዕይ በይፋ በተከፈተበት ወቅት ነው።
የንባብ ባህልን ለማበረታታት እና እውቀትን ለትውልድ ለማድረስ በተዘጋጀው በዚህ አውደ-ርዕይ ላይ ከ47 በላይ የመጻሕፍት አሳታሚዎችና አከፋፋዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ በሁሉም የእውቀት ዘርፎች የሚያተኩሩ በርካታ ነባርና አዳዲስ መጻሕፍት ለአንባቢያን በቅናሽ ዋጋ ቀርበዋል። በቆይታውም አዳዲስ መጻሕፍት እንደሚመረቁ ታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬስ ሚና እና የወደፊት አቅጣጫ አውደ-ርዕዩን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ከ50 ዓመታት በላይ ባስቆጠረው ታሪኩ ጥራት ያላቸውን መጻሕፍት በማሳተምና በማከፋፈል በትውልድ መካከል የእውቀት ትስስር እየፈጠረ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬስ አቅም በማጎልበት እና ዘመኑ በፈጠራቸው የገበያ አማራጮች በመጠቀም ተደራሽነቱን የሚያሰፉ ስራዎች ተከናውነዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል አክለውም፣ ከተለዋዋጩ የዘመኑ ሁኔታ ጋር አብሮ በመራመድ ዘመን ተሸጋሪ የሆኑ ሥራዎችን መስራትና በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
What's Your Reaction?