በ667 ማዕከላትና በ6 ዙር የሚሰጠው የዲጂታል ሽግግር ፈተና
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በታላቅ ዝግጅት ለመስጠት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መደረሱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በታላቅ ዝግጅት ለመስጠት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መደረሱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ በ667 የፈተና ማዕከላት ላይ የሚሰጥ ይሆናል። ለዚህም ሲባል 97 ዩኒቨርሲቲዎች እና 570 የክልል ማዕከላት ዝግጁ ተደርገዋል።
ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በሚሰጠው በዚህ ወሳኝ ፈተና ላይ ለመቀመጥ በአጠቃላይ 564,219 ተማሪዎች ተመዝግበዋል።
ከተፈታኞቹ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች ሲሆኑ ቁጥራቸው 306,964 ይደርሳል። በቀሪው 257,255 የወንበር ቁጥር ላይ ደግሞ የማኅበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።
ፈተናው በኢንተርኔት (ኦንላይን) እና በ6 ዙር ይካሄዳል።
የዘንድሮውን ፈተና ለየት የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በበይነ መረብ (Online) ለመስጠት ታላቅ ዝግጅት መደረጉ ነው። ይሁን እንጂ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ውስንነት ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተማሪዎች በወረቀት እንደሚፈተኑ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
የፈተናው ሂደት ያለምንም መጨናነቅና በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ ሂደቱ በስድስት ዙር የተከፋፈለ ሲሆን፣ ማኅበራዊ ሳይንስ በሦስት ዙር እንዲሁም ተፈጥሮ ሳይንስ በሦስት ዙር ተከፋፍለው ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።
What's Your Reaction?