ሎሚ ዜና ❌ የሀሰተኛ ዜና ማጣሪያ

"የብሪክስ ስብሰባ ፈረሰ እና የአሜሪካ-ኢራን ጦርነት"፦ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው የሀሰተኛ ዜና ሰሞኑን በተለያዩ ድረ-ገጾች እና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ "የብሪክስ ስብሰባ በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን ጦርነት ምክንያት ያለ ስምምነት ፈረሰ" የሚል ሰፊ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል።

May 18, 2026 - 12:57
May 21, 2026 - 20:00
 0  2
ሎሚ ዜና ❌ የሀሰተኛ ዜና ማጣሪያ

"የብሪክስ ስብሰባ ፈረሰ እና የአሜሪካ-ኢራን ጦርነት" በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው የሀሰተኛ ዜና

ሰሞኑን በተለያዩ ድረ-ገጾች እና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ "የብሪክስ ስብሰባ በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን ጦርነት ምክንያት ያለ ስምምነት ፈረሰ" የሚል ሰፊ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል። ሎሚ ዜና ጉዳዩን አጣርቶ የሚከተለውን እውነተኛ መረጃ አዘጋጅቷል፦"ባለፈው የካቲት 28 አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ሰንዝረው ጦርነት ተጀምሯል፣ የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ተዘግቷል፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቻይና በመሆናቸው የብሪክስ ስብሰባ ተበላሽቷል" የሚል የሀሰተኛ መረጃ በተላያየ ማህበራዊ ኢዲያ ሲሰራጭ ተምልክተናል

ይህ መረጃ ፍጹም የፈጠራ  ወሬ ነው። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተጀመረ ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ጦርነት የለም። የባህር መስመሮች ክፍት ናቸው፣ የአለም የነዳጅ ገበያም በተለመደው ሁኔታ ላይ ይገኛል። የብሪክስ/ BRICS ጥረት አባል ሀገራትን የጋራ ተጠቃሚነት ማሳደግ ሲሆን፣ እንደተባለው በጦርነት ምክንያት የፈረሰ ስብሰባ የለም። የሀገራቱ መሪዎች ጉባኤም በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት በህንድ ይካሄዳል።

ማሳሰቢያ፦ ተከታታዮች መሰል ያልተረጋገጡ እና የተጋነኑ የጦርነት ወሬዎችን እንዳያምኑ እና ከመጋራት እንዲቆጠቡ ሎሚ ዜና ያሳስባል።

 ሎሚ ዜናእውነተኛ መረጃ ለሁሉም!

 

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow