ቻይና በሰማይ የሚበር የመኪና ቴክኖሎጂ ተቋሟ የሙከራ ማዕከል ጀመረ
በደቡብ ቻይና ጓንግዶንግ ግዛት ውስጥ መኪናዎችን በምድር ላይ ብቻ ሳይሆን በሰማይም ጭምር ለመፈተሽ የሚያስችል "የደቡባዊ ስማርት የተሳሰሩ አዳዲስ የኃይል ማመንጫ ተሽከርካሪዎች የሙከራ ማዕከል" ሥራ መጀመሩ ተገለጠ፡፡
በደቡብ ቻይና ጓንግዶንግ ግዛት ውስጥ መኪናዎችን በምድር ላይ ብቻ ሳይሆን በሰማይም ጭምር ለመፈተሽ የሚያስችል "የደቡባዊ ስማርት የተሳሰሩ አዳዲስ የኃይል ማመንጫ ተሽከርካሪዎች የሙከራ ማዕከል" ሥራ መጀመሩ ተገለጠ፡፡ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ብሔራዊ ደረጃ ያለው ይኸው የመንገድ እና የአየር የተቀናጀ የሙከራ ቦታ፣ በትራንስፖርትና በቴክኖሎጂ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ተቋም ሆኗል፡፡
ማዕከሉ በ8,600 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈና ወደ 100 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የጸደቀ የአየር ክልል ያለው ሲሆን፣ ማንኛውንም ዓይነት የተሽከርካሪ ሙከራዎችን በተሟላ ሁኔታ ለማከናወን ታስቦ የተገነባ ነው፡፡ ተቋሙ በዋናነት ለተለመዱ መኪኖች ብቃት ማረጋገጫ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለተሳሰሩ ስማርት ተሽከርካሪዎች ፍተሻ እና ወደፊት አገልግሎት ላይ ለሚውሉ "የሚበሩ መኪኖች" የዝቅተኛ ከፍታ በረራ ሙከራዎችን ለማድረግ ያገለግላል፡፡
ለዚህም ይረዳ ዘንድ 8,500 ሜትር ርዝመት ያለው የከፍተኛ ፍጥነት የክበብ መንገድ፣ 300 ሜትር ዲያሜትር ያለው ተንቀሳቃሽ ፕላዛ፣ 1,800 ሜትር የብቃት ማሳያ መንገድ እና መኪኖቹ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲፈተሹ የሚያስችሉ 34 ልዩ ልዩ የገጽታ ዓይነቶችን ያካተተ ሰፊ የመንገድ አውታር በውስጡ አካትቷል፡፡
What's Your Reaction?