የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ጤና ማዕከል ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስነልቦና ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ጋር በመተባበር በ2017 ዓ.ም የተቋቋመው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ጤና እና የስነልቦና ድጋፍ ማዕከል፣ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘርፈ-ብዙ እገዛ ማድረጉን አስታውቋል።
ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ጋር በመተባበር በ2017 ዓ.ም የተቋቋመው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ጤና እና የስነልቦና ድጋፍ ማዕከል፣ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘርፈ-ብዙ እገዛ ማድረጉን አስታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ፀጋይ ተክለሀይማኖት እንደገለጹት፤ ማዕከሉ ቁርጠኛ በሆኑ ባለሙያዎችና በሰለጠኑ ሰራተኞች አማካኝነት የምክር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 6626 በተባለው የነጻ የስልክ መስመር አማካኝነት ለ2 መቶ 86 ሰዎች የርቀት ድጋፍ መስጠት ችሏል።
ይህ አገልግሎት በተለይም ማህበረሰቡ ከግጭት ማግስት የሚያጋጥሙትን ዘላቂ የስነልቦና ጠባሳዎች ተቋቁሞ እንዲያልፍ፣ የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት እንዲመራ ለማስቻል አልሞ የሚሰራ መሆኑን የጠቀሱት ሜዲካል ዳይሬክተሩ፤ ህክምና ፈላጊዎች ወደ ማዕከሉ በአካል በመምጣት ወይም ባሉበት ሆነው በነጻ ስልክ መስመሩ በመጠቀም የአእምሮ ደህንነታቸውን ሊጠብቁ እንደሚችሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
What's Your Reaction?