ኢትዮጵያ በብሪክስ፤ የአለም አቀፍ አስተዳደር ማሻሻያ እንዲደረግ ጠየቀች
በ2026ቱ የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ነባሩ የዓለም አቀፍ አስተዳደር ሥርዓት በአስቸኳይ እንዲሻሻልና ፍትሐዊነት እንዲሰፍን ጠንካራ ጥሪ አቅርቧል።
በ2026ቱ የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ነባሩ የዓለም አቀፍ አስተዳደር ሥርዓት በአስቸኳይ እንዲሻሻልና ፍትሐዊነት እንዲሰፍን ጠንካራ ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያን አቋም በሦስት ዋና ዋና ነጥቦች መመልከት ይቻላል፦
የፖለቲካ ውክልና፦ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ የአፍሪካን የጋራ አቋም (ኤዙልዊኒ ስምምነት) መሠረት ያደረገ መሆን እንዳለበትና የአህጉሪቱን ተወካዮች የመምረጥ መብት ለአፍሪካውያን ለራሳቸው እንዲተው አሳስቧል።
የፋይናንስ ፍትሐዊነት፦ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እንደ ሀገራት የኢኮኖሚ ድርሻ የውክልና ማስተካከያ እንዲያደርጉ፣ የዕዳ ሽግሽግ አሠራሮች እንዲሻሻሉና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ድጋፍ እንዲኖር ጠይቋል።
የንግድ ሥርዓት፦ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በድርድር ላይ መሆኗን የጠቀሰው ልዑኩ፤ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት "በአካባቢ ጥበቃ" ስም ከሚጣሉ ረቂቅ የንግድ ገደቦች ሊጠበቁ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጿል።
ኢትዮጵያ በብሪክስ መድረክ የደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ድምፅ በመሆን፣ ከኮታ ማስተካከያ ባለፈ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲመጣ እየወተወተች ነው።
What's Your Reaction?