የአርሰናል እና የ "Visit Rwanda" ስምምነት እውነታ
አርሰናል እና የ "Visit Rwanda" ስምምነት እውነታየአርሰናል እና የ "Visit Rwanda" እውነታው ምንድን ነው?በአርሰናል ማሊያ እጅጌ ላይ የሚገኘው የ "Visit Rwanda" የቱሪዝም ማስተዋወቂያ ስምምነት መቋረጡን የሚገልጹ ወሬዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወሩ ይገኛሉ። ሎሚ ዜና በጉዳዩ ዙሪያ ያሉትን ዋና ዋና እውነታዎች እንደሚከተለው አጠናቅሯል፦
ሎሚ ስፖርት፡ የአርሰናል እና የ "Visit Rwanda" እውነታው ምንድን ነው?
በአርሰናል ማሊያ እጅጌ ላይ የሚገኘው የ "Visit Rwanda" የቱሪዝም ማስተዋወቂያ ስምምነት መቋረጡን የሚገልጹ ወሬዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወሩ ይገኛሉ። ሎሚ ዜና በጉዳዩ ዙሪያ ያሉትን ዋና ዋና እውነታዎች እንደሚከተለው አጠናቅሯል፦
የወሬዎች መነሻ የየፖለቲካ ግፊት ሲሆን ይህ ስምምነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተለይም በእንግሊዝ እና በሩዋንዳ መካከል ከነበረው የስደተኞች ጉዳይ ጋር ተያይዞ የተለያዩ የእንግሊዝ ፖለቲከኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አርሰናል ውሉን እንዲያቋርጥ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን የሚሰሙት ወሬዎችም ከነዚህ ተከታታይ ግፊቶች የሚመነጩ ናቸው።
ያም ሆኖ Visit Rwanda የውል ዘመን አርሰናል እና የሩዋንዳ ቱሪዝም ቦርድ እ.ኤ.አ በ2021 ላይ ውላቸውን ለተጨማሪ 4 ዓመታት አድሰውት የነበር ሲሆን ይህ ውል እስከ 2025/2026 የውድድር ዘመን ድረስ ዘልቆዋል.፣ በአሁኑ ወቅት ውሉ በስምምነት መሰረት መጠናቀቁ እንጂ በድንገት "ተሰረዘ" የሚያሰኝ ይፋዊ መረጃ የለም . እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ከአርሰናል እግር ኳስ ክለብም ሆነ ከሩዋንዳ መንግሥት በኩል ስምምነቱ መቋረጡን የሚገልጽ ምንም ዓይነት ይፋዊ መግለጫ አልወጣም።
ሎሚ ዜና
What's Your Reaction?