ኢትዮጵያ በትንባሆ ቁጥጥር ረገድ "የተጨባጭ ውጤት" ባለቤት መሆኗ ተነገረ

​ኢትዮጵያ "ለኒኮቲንና ለትንባሆ ሱሰኝነት አጋላጭ የሆኑ ስልቶችን እናጋልጥ" በሚል መሪ ቃል የዓለም ከትንባሆ ጭስ ነፃ ቀንን ለ34ኛ ጊዜ ስታከብር፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በቁጥጥሩ ረገድ ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸውን አበስሯል።

May 15, 2026 - 12:49
 0  0
ኢትዮጵያ በትንባሆ ቁጥጥር ረገድ "የተጨባጭ ውጤት" ባለቤት መሆኗ ተነገረ

​ኢትዮጵያ "ለኒኮቲንና ለትንባሆ ሱሰኝነት አጋላጭ የሆኑ ስልቶችን እናጋልጥ" በሚል መሪ ቃል የዓለም ከትንባሆ ጭስ ነፃ ቀንን ለ34ኛ ጊዜ ስታከብር፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በቁጥጥሩ ረገድ ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸውን አበስሯል።

 ባለሥልጣኑ በ8 ክልሎች አስተባባሪ ኮሚቴዎችን በማዋቀርና 900 ሺህ የሚጠጉ ተቋማት ላይ የፍተሻና የግንዛቤ ሥራዎችን በመስራት ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን ገልጾ፣ ለማጨስ የተዘጋጁ የትንባሆ ቅጠሎችና ሲጋራዎችን ማስወገድ መቻሉንም ጠቁሟል። 

የትንባሆ ኢንዱስትሪውን አሳሳች ማስታወቂያዎች ለመመከትና የፖሊሲ ክፍተቶችን ለመድፈን ቃል የገባው ባለሥልጣኑ፣ መገናኛ ብዙኃንና የሲቪል ማኅበራት ለሕዝቡ ትክክለኛውን የጤና መረጃ በማድረስ ንቅናቄውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርቧል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow