የለንደን ሰማይ ስር የትኬት ዋጋ  ንሯል!  

​የ22 ዓመቱ የናፍቆት እምባ አብቅቶ መድፈኞቹ ታሪክ ሊሰሩ ጥቂት ሰዓታት ቀራቸው። ነገር ግን ያንን ታሪካዊ ቅጽበት በዓይን ለማየት የሚከፈለው ዋጋ አስደንጋጭ ሆኗል!

May 21, 2026 - 11:13
 0  4
የለንደን ሰማይ ስር የትኬት ዋጋ  ንሯል!  

​የ22 ዓመቱ የናፍቆት እምባ አብቅቶ መድፈኞቹ ታሪክ ሊሰሩ ጥቂት ሰዓታት ቀራቸው። ነገር ግን ያንን ታሪካዊ ቅጽበት በዓይን ለማየት የሚከፈለው ዋጋ አስደንጋጭ ሆኗል!
​ሻምፒዮኑ አርሰናል የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ የክብር ዋንጫ በይፋ የሚያነሳበትና ከሜዳው ውጪ ከክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርገው የመጨረሻው የዓመቱ ጨዋታ የዓለምን ትኩረት ስቧል። 

ታሪካዊውን የዋንጫ ስነ-ስርዓት በስታዲየም ተገኝቶ ለመታደም የሚደረገው ፍልሚያ ሜዳው ላይ ካለው ጨዋታ የባሰ ብርቱ እየሆነ ነው።
​የአርሰናል ደጋፊዎች ዋንጫውን በደስታ ለመቀበል ባላቸው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ፣   Online የሚሸጡ የመልሶ ሽያጭ ትኬቶች ዋጋ ሰማይ ነክቷል!

የ22 ዓመታት ትዕግስት ፍሬ ​መድፈኞቹ ከፈረንሳዊው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር "የማይሸነፉት ስብስብ" ታሪካዊ ድል በኋላ፣ ለተከታታይ 22 ዓመታት የናፈቃቸውን የፕሪሚየር ሊግ ዘውድ እሁድ ዕለት በይፋ ይረከባሉ።
​ይህንን ትውልድ ተሻጋሪ ታሪክ በቦታው ተገኝቶ ለመመስከር ደጋፊው ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን የትኬቱ ገበያ ማሳያ ሆኗል። ለንደን በአርሰናል ቀይ እና ነጭ ቀለማት አብባለች፤ እሁድን ለመቀበልም ቀን እየተቆጠሩ ነው።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow