የምያንማሩ የ10 ሚሊዮን ዶላር የሳይበር አደን እና የታገቱት ኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታ

በምያንማር የጫካ ኮምፓውንዶች ውስጥ የታገቱት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እና የአሜሪካ የ10 ሚሊዮን ዶላር አደን

May 24, 2026 - 09:39
 0  1
የምያንማሩ የ10 ሚሊዮን ዶላር የሳይበር አደን እና የታገቱት ኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታ

አዲስ አበባ በአሜሪካ መንግስት እና በዓለም አቀፍ የህግ አስከባሪዎች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገበት የሚገኘው የደቡብ ምስራቅ እስያ የሳይበር ማጭበርበሪያ መረብ፣ በርካታ ወጣት ኢትዮጵያውያን የኮምፒውተር ባለሙያዎችን ለከፋ እገታ እና ለባርነት እየዳረገ መሆኑ ታወቀ።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (State Department) በምያንማር ,በርማ የጫካ ቀጠናዎች ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን አፍኖ በማስገባት የሳይበር ስርቆት ለሚያካሂደው የወንጀለኞች ቡድን መሪዎች መያዣ ወይም መረጃ ለሚሰጥ አካል እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ማዘጋጀቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት፣ ጉዳዩ በቀጥታ ከኢትዮጵያውያን ወጣቶች ህይወት ጋር የተያያዘ መሆኑ ስጋቱን አግዝፎታል።

 የአሳማ እርባታእና የኢትዮጵያውያን ስቃይ

ቀደም ሲል በእስያ ሀገራት ዜጎች ላይ ብቻ ያተኩሩ የነበሩት እነዚህ የቻይና ሲንዲኬት (የወንጀል መረብ) አባላት፣ አሁን ላይ ፊታቸውን ወደ ምስራቅ አፍሪካ በተለይም ወደ ኢትዮጵያ ማዞራቸውን የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ሪፖርቶች ያመለክታሉ።ወንጀለኞቹ በቴሌግራም  እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይበታይላንድ ወይም በዱባይ ከፍተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት የቴክኖሎጂ (IT) እና የዳታ ሶፍትዌር ስራ አለበማለት የሀሰት ማስታወቂያዎችን ያወጣሉ።

 በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ስራ አጥተው የሚንከራተቱ የወረቀት ዲግሪ ያላቸው የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪዎች ለዚህ የተንኮል ወጥመድ ዋነኛ ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ።ወጣቶቹ ታይላንድ ባንኮክ እንደደረሱ ፓስፖርታቸው እና ስልኮቻቸው በሃይል የሚቀሙ ሲሆን፣ ከዚያም በታጣቂዎች ታጅበው በምያንማር ድንበር ላይ ወደሚገኙት እና በታጠቁ አማጺያን ወደሚጠበቁት እንደ "ኬኬ ፓርክ" (KK Park) እና "ሹንዳ" (Shunda Compound) ወደተባሉ አስፈሪ ወታደራዊ መሰል ግቢዎች ይወሰዳሉ።

 በእነዚህ ኮምፓውንዶች ውስጥ የታገቱ ወጣቶች በቀን እስከ 19 ሰዓታት ያለ እረፍት በሀሰተኛ የሶሻል ሚዲያ አካውንቶች ሰዎችን እያታለሉ የክሪፕቶክረንሲ ኢንቨስትመንት (Cryptocurrency) እንዲዘርፉ ይገደዳሉ። የተሰጣቸውን የገንዘብ መጠን ካላስገቡ ግን በኤሌክትሪክ ንዝረት መመታት፣ በአሰቃቂ ሁኔታ መገርረፍ እና ለቀናት በረሃብ መቀጣት የዕለት ተዕለት እጣ ፈንታቸው መሆኑን ከተፈቱት መካከል የተገኙ ምስክሮች ይናገራሉ።

 የስጋት ቀጠናው ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ ነው

ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ የሩቅ ስጋት እንዳይደል የሚያሳየው ሌላው አሳሳቢ መረጃ፣ የወንጀል መረቦቹ አሁን ላይ መሰረታቸውን ወደ አፍሪካ ለማዛወር እያደረጉት ያለው ጥረት ነው።በምያንማር እና በካምቦዲያ መንግስታት እንዲሁም በአሜሪካ ልዩ የሳይበር ግብረ-ኃይል (Scam Center Strike Force) እየተወሰደባቸው ያለው ጠንካራ እርምጃ ሳቢያ፣ የሳይበር ወንጀለኞቹ ማዕከላቶቻቸውን ህግ እና ቁጥጥር ባልጠናባቸው የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ በድብቅ መገንባት ጀምረዋል።

 እንደ Global Initiative Against Transnational Organized Crime 2026 የቅርብ ጊዜ ጥናት ከሆነ፣ እነዚህ ሲንዲኬቶች በምስራቅ አፍሪካ ፈጣን የኢንተርኔት ግንኙነት እና ከፍተኛ የተማረ ስራ አጥ ወጣት ያላትን ኢትዮጵያን እንደ አዲስ የወንጀል መደበቂያ ማዕከል (Cyber Scam Hub) አድርገው ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል።የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጥቂት ወጣቶችን ማስለቀቅ የቻለ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ በምያንማር ጫካዎች ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በባርነት ህይወታቸው እየቀጨ ይገኛል።

 በመሆኑም ማህበረሰባችን በተለይም ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ በሚለቀቁ "የእስያ ሀገራት የቴክኖሎጂ ስራዎች" ስም ከተሸሸጉ ህገ-ወጥ የሰዎች አጓጓዦች እና አጋቾች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ሎሚ ኒውስ በጥብቅ ያሳስባል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow