ከዓለም ዋንጫው ድምቀት ጀርባ ያለው ስውር አደጋ - ''የሰው አጋቾች የተዘረጋው ወጥመድ"

የ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ ሊጀመር ጥቂት ጊዜያት ሲቀሩት፣ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ተቋማት ስለ ሰው ዝውውር (human trafficking) ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

May 12, 2026 - 10:21
 0  2
ከዓለም ዋንጫው ድምቀት ጀርባ ያለው ስውር አደጋ - ''የሰው አጋቾች የተዘረጋው ወጥመድ"
ከዓለም ዋንጫው ድምቀት ጀርባ ያለው ስውር አደጋ -'' የሰው አጋቾች የተዘረጋው ወጥመድ" የ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ ሊጀመር ጥቂት ጊዜያት ሲቀሩት፣ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ተቋማት ስለ ሰው ዝውውር (human trafficking) ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። እንደ ዓለም ዋንጫ ያሉ ግዙፍ ዝግጅቶች በወንጀለኞች አማካኝነት ሰዎችን ለማጭበርበርና ለዝሙት ወይም ለጉልበት ብዝበዛ ለመዳረግ እንደ ምቹ አጋጣሚ ይወሰዳሉ። ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ወደ አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ይጎርፋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት በዚህ ወቅት፣ ወንጀለኞች በተለይ ከአፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ የሚመጡ ሰዎችን በሐሰተኛ የሥራ ዕድል ጥሪ ሊያታልሉ ተብሎዋል .የ2026 ዓለም ዋንጫ ደጋፊዎች ወደ አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት ሊያውቁት የሚገባ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ - የሰው አጋቾች የተዘረጋው ወጥመድ የተዘረጋ በምሆኑ አስፍላጊውን ጥንቃቅ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቶዋል የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት በጥርጣሬ ሊታዩ የሚገባቸውን የገንዘብ እንቅስቃሴዎች እንዲከታተሉ ታዘዋል። ደጋፊዎች ከታመኑ የፊፋ ወኪሎች ውጭ በሚቀርቡ "ረካሽ" የጉዞ ጥቅሎች እንዳይታለሉ ይመከራሉ። ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ውድድሩ በሰላም እንዲጠናቀቅና ንፁሃን ዜጎች ለከፋ በደል እንዳይጋለጡ ለማድረግ ነው። ማንኛውም ተጓዥ ከመሄዱ በፊት የሆቴልና የጉዞ ሰነዶቹን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይኖርበታል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow