በትልልቅ ፕሮጀክቶች የጎለበተው የኢትዮጵያ ቱሪዝም፤ የጎብኚዎችን ቁጥር 1.3 ሚሊዮን አደረሰ

ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላምና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ በማድረግ ሰፊ መዋቅራዊ ለውጦችን እያስመዘገበች ትገኛለች።

May 18, 2026 - 10:43
May 18, 2026 - 10:59
 0  2
 በትልልቅ ፕሮጀክቶች የጎለበተው የኢትዮጵያ ቱሪዝም፤ የጎብኚዎችን ቁጥር 1.3 ሚሊዮን አደረሰ

ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላምና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ በማድረግ ሰፊ መዋቅራዊ ለውጦችን እያስመዘገበች ትገኛለች። ዘርፉን ለማሳደግ ለ16 ዓመታት የቆየው የቱሪዝም ፖሊሲ ተሻሽሎ በሚኒስቴር ደረጃ እንዲደራጅ የተደረገ ሲሆን፣ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ስትራቴጂ (MICE) ተቀርጾ መተግበሩና የኢ-ቪዛ ዲጂታል አሠራር መዘርጋቱ የቱሪስት ፍሰቱን በእጅጉ አቀላጥፎታል። 

በተለይም እንደ “ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ኮሪደር ልማት” ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ ሀብትን ከልማት ጋር በማስተሳሰር ለሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
​በዚህም መሠረት እንደ እንጦጦ፣ ወንጪ፣ ሃላላ ኬላ እና ኮይሻ ያሉ አዳዲስ መዳረሻዎች ወደ ሥራ በመግባታቸው የቱሪስቶች ቁጥር ከ781 ሺህ ወደ 1.3 ሚሊዮን ማደጉን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል። ይህ ስኬት የውጭ ምንዛሪ ገቢንና የሥራ ዕድልን ከማማረቱም በላይ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት አዳዲስ ቅርሶችን በዩኔስኮ በማስመዝገብ የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ሽልማትንም አስገኝቷል። 

ወደፊትም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀምና መሠረተ ልማትን በማስፋፋት የቱሪስት ፍሰቱን እስከ 7.3 ሚሊዮን ለማድረስና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ሰፊ ራዕይ ተቀምጦ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow