"የዓለም ዋንጫው ለነሱ እንጂ ለኛ አይደለም"

ባለፈው መጋቢት ወር የኢራቅ እግር ኳስ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ፥ አብዱላህ አድናን የተባለ ደጋፊ በአሜሪካ ለሚደረጉት ጨዋታዎች ትኬት ቢቆርጥም ቪዛ ማግኘት አልቻለም። 

Jun 8, 2026 - 16:39
 0  1
"የዓለም ዋንጫው ለነሱ እንጂ ለኛ አይደለም"

ባለፈው መጋቢት ወር የኢራቅ እግር ኳስ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ፥ አብዱላህ አድናን የተባለ ደጋፊ በአሜሪካ ለሚደረጉት ጨዋታዎች ትኬት ቢቆርጥም ቪዛ ማግኘት አልቻለም። 

የቢቢሲ መረጃ እንደሚያሳየው በውድድሩ ከሚሳተፉ ሀገራት የሩብ ያህሉ ደጋፊዎች የአሜሪካ የጉዞ እገዳና ጥብቅ ገደቦች እየገጠሟቸው ነው።

ለኢራቃውያን ዋነኛ እንቅፋት የሆነው በአሜሪካና በኢራን መካከል ከተቀሰቀሰው ጦርነት በኋላ አሜሪካ በኢራቅ የቪዛ አገልግሎት ማቋረጧ ሲሆን፥ አብዱላህ ቪዛ ፍለጋ ወደ ዮርዳኖስ ተጉዞም የሀገሩ ዜጋ ባለመሆኑ ሳይሳካለት ቀርቷል።

በሌላ በኩል በፕሬዝዳንት ትራምፕ የጉዞ እገዳ ምክንያት በዓለም ዋንጫው ላይ የሚሳተፉት የሄይቲ፣ ኢራን፣ ሴኔጋል እና አይቮሪ ኮስት ዜጎች ደጋፊዎች የሚሆኑበትን የጎብኝ ቪዛ እንዳያገኙ ተከልክለዋል።

የአይቮሪ ኮስት ደጋፊው ጁሊየን ኩዋዲዮ ይህንን ገደብ "የማግለል ድርጊት" ሲል ኮንኖታል።

የአሜሪካ ባለስልጣናት እ.ኤ.አ. በ2024 በትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ቃል በተገባው መሰረት ህገ-ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር አሰራሩ ጥብቅ መሆን እንዳለበት ቢገልጹም፥ አሠራሩ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ደጋፊዎች ዘንድ "የዓለም ዋንጫው ለነሱ እንጂ ለኛ አይደለም" የሚል ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow