የራባት ጎዳናዎች በኢትዮጵያ ባንዲራ አሸበረቁ!

"ድል ለኢትዮጵያ! በሞሮኮ መሬት ላይ የተመዘገበ ታሪካዊ የበላይነት" ዛሪ  በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው የራባት ማራቶን ውድድር፣ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የራባትን ጎዳናዎች የድል አደባባይ አድርገውታል። በሁለቱም ፆታዎች ከመጀመርያ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በአስደናቂ ሁኔታ በመቆጣጠር፣ ዓለምን ያስገረመ ፍጹም የበላይነትን አስመዝግበዋል።

May 11, 2026 - 15:33
 0  5
የራባት ጎዳናዎች በኢትዮጵያ ባንዲራ አሸበረቁ!

"ድል ለኢትዮጵያ! በሞሮኮ መሬት ላይ የተመዘገበ ታሪካዊ የበላይነት"

ዛሪ  በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው የራባት ማራቶን ውድድር፣ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የራባትን ጎዳናዎች የድል አደባባይ አድርገውታል። በሁለቱም ፆታዎች ከመጀመርያ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በአስደናቂ ሁኔታ በመቆጣጠር፣ ዓለምን ያስገረመ ፍጹም የበላይነትን አስመዝግበዋል።

የወንዶች ምድብ፦ የቦኪ ዲሪባ እና የጓደኞቹ ድል

በወንዶች የረጅም ርቀት ፍልሚያ፣ አትሌት ቦኪ ዲሪባ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ፍጥነት በማሳየት ርቀቱን 2 ሰዓት 7 ደቂቃ 52 ሴኮንድ አጠናቆ የወርቅ ሜዳልያውን ለብሷል። ድሉን ይበልጥ ያደመቁት አትሌት ቶልቻ ተፈራ (2) እና አትሌት ጫሉ ዴሶ (3) በመሆን መድረኩን ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ አድርገውታል።

የሴቶች ምድብ፦ የአለምፀሐይ እና ጉዋደኞችዋ ገድል

በሴቶች ምድብም ታሪኩ ተመሳሳይ ነበር፤ አትሌት አለምፀሐይ አሰፋ 2 ሰዓት 25 ደቂቃ 3 ሴኮንድ ቀዳሚ በመሆን ድል ቀንቷታል። አትሌት መሰረት አበባየው እና አትሌት ስራነሽ ይርጋ ተከታትለው በመግባት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የኢትዮጵያን የበላይነት አረጋግጠዋል።በተጨማሪም አትሌት ጌጤ ጁካለ 5 እንዲሁም አትሌት ኩሊ ጪምዴሳ 6 ደረጃን በመያዝ ውድድሩን በስኬት አጠናቀዋል።

ይህ ድል ኢትዮጵያ በማራቶን ያላትን የማይናወጥ የአንበሳነት ድርሻ በድጋሚ ለዓለም ያሳየችበት ነው። በሁለቱም ፆታዎች 1ኛ፣ 2 እና 3 ወጥቶ መድረኩን መቆጣጠር ብርቅ እና ታሪካዊ ክስተት ነው።

ሎሚ ዜና፦ የአትሌቶቻችንን የድል ዜና እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያደርሳል!

#LomiiNews #RabatMarathon #EthiopianAthletes #Victory #Ethiopia #የራባትማራቶን #ታሪካዊድል #ሎሚዜና

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow