አሜሪካ በደቡባዊ ኢራን የ ሚሳይል ማረፊያዎችን እና የጦር ጀልባዎችን አወደመች
የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ በደቡባዊ ኢራን በምትገኘው ስልታዊዋ የባንደር አባስ (Bandar Abbas) የወደብ ከተማ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።
በኳታር ዶሃ የሰላም ንግግር እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ በደቡባዊ ኢራን በምትገኘው ስልታዊዋ የባንደር አባስ (Bandar Abbas) የወደብ ከተማ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።
አሜሪካ ጥቃቱን የፈጸመችው "እራሷን ለመከላከል" መሆኑን ገልጻለች። የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ የባህር ላይ ፈንጂዎችን ለመቅበር ሲሞክሩ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች እና የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ላይ ኢላማ አድርጎ የነበረ የፎቶን ሚሳይል ማረፊያ መውደማቸው ተገልጿል። በዚሁ ጥቃት ቢያንስ 4 ሰዎች መሞታቸውን የኢራን መንግስታዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ሁለቱ ሀገራት የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማራዘም በዶሃ ድርድር ላይ ባሉበት ወቅት ነው። አሜሪካ የዩራኒየም ማበልጸጊያ ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም የያዘች ሲሆን፣ የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ) ክፍት ሆኖ እንዲቀጥል የኃይል እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።
What's Your Reaction?