የኢራን ብሔራዊ ቡድን በፖለቲካ ውጥረት ምክንያት ማረፊያውን  ቀየ

May 26, 2026 - 10:13
 0  2
የኢራን ብሔራዊ ቡድን በፖለቲካ ውጥረት ምክንያት ማረፊያውን  ቀየ

በሊባኖስ እና በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ከፍተኛ የጦርነት ውጥረት ምክንያት የኢራን ብሔራዊ ቡድን በዩናይትድ ስቴትስ አሪዞና ሊያደርገው የነበረውን የዓለም ዋንጫ የልምምድ ካምፕ (Base Camp) በድንገት ሰርዟል።የኢራን ብሒርዊ ቡድን አዲሱ ማረፊያ  ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ ወደ ሜክሲኮዋ የድንበር ከተማ ቲጁአና  እንዲቀይር በይፋ ፈቅዷል። የሜክሲኮዋ ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሼይንባም ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ የኢራን ተጫዋቾች በግዛቷ ላይ እንዲያድሩ ስላልፈለገች ወደ ሜክሲኮ እንዲመጡ መጠየቋን እና ሀገራቸው ይህንን በደስታ መቀበሏን አረጋግጠዋል። ሆኖም ቡድኑ የምድብ ጨዋታዎቹን አሜሪካ ውስጥ (ሎስ አንጀለስ እና ሲያትል) ማድረጉን ይቀጥላል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow