ኢትዮ ቴሌኮም የቀጣዩ አድማስ 2028 ስትራቴጂ የመጀመሪያ ዓመት ትግበራውን በከፍተኛ ስኬት አጠናቀቀ
የኢትዮ ቴሌኮም የ2018 በጀት ዓመት የቀጣዩ አድማስ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 የሶስት ዓመት ስትራቴጂ የመጀመሪያ ዓመት ትግበራ በሁሉም የሥራ ክንውንና የፋይናንስ መለኪያዎች ከፍተኛ ስኬት በማስመዝገብ መጠናቀቁ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም የ2018 በጀት ዓመት የቀጣዩ አድማስ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 የሶስት ዓመት ስትራቴጂ የመጀመሪያ ዓመት ትግበራ በሁሉም የሥራ ክንውንና የፋይናንስ መለኪያዎች ከፍተኛ ስኬት በማስመዝገብ መጠናቀቁ ተገልጿል።
ኩባንያው የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን፣ የዲጂታል አካታችነትንና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስመዝገብ ያለመ እድገት፣ ትራንስፎርሜሽን፣ ውጤታማነት እና ጽናት በሚሉ አራት ዋና ዋና አዕማድ በተዋቀረው የስትራቴጂካዊ ኳድራንት ማዕቀፍ አማካኝነት በስርዓት ሲተገብር ቆይቷል።
በእንቅስቃሴውም ከመደበኛ የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ወደ ሁሉን አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋም የመሸጋገር ጉዞውን በተሳካ ሁኔታ የጀመረ ሲሆን፣ ከመሠረታዊ የግንኙነት አገልግሎት ባለፈ ወደ ክላውድ መፍትሔዎች፣ በቴሌብር አማካኝነት ወደ ዲጂታል ሞባይል ፋይናንስ፣ ወደ ኢንተርፕራይዝ መፍትሔዎች እና በሰው ሠራሽ አስተውሎት ወደታገዙ ፕላትፎርሞች በመስፋፋት የዜጎችን፣ የንግዱን ማኅበረሰብና የመንግሥት ተቋማትን አሰራር ማዘመን ችሏል።
ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ስትራቴጂካዊ ውጥን ለሀገራዊው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይና ለተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን፣ በቴሌኮም እና ዲጂታል መሠረተ ልማት ላይ የሚደረገውን ቀጣይነት ያለው ኢንቨስትመንት በማጠናከር ድንበር ተሻጋሪ አገልግሎቶችን ለመስጠት፣ አህጉራዊ ትብብርን በማጎልበት የዲጂታል አፍሪካ 2063 ጉዞን ለማፋጠንና በቀጠናው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል እየሰራ ይገኛል።
What's Your Reaction?