የአየር ንብረት ለውጥ በምስራቅ አፍሪካ የውሃና የኃይል ዘርፍ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ እና ቀጣናዊ ሁነቶች

አዲስ አበባ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ያጋጠመው ዝቅተኛ የዝናብ መጠን በሃገሪቱ የኃይል ማመንጫ ግድቦች የውሃ መጠን ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) የደረቅ ወራትን የኃይል አቅርቦት ታሳቢ ያደረገ ጥብቅ የውሃ አጠቃቀም አሰራር መዘርጋቱን አስታወቀ።

Sep 4, 2026 - 13:58
 0  2

ተቋሙ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፣ ይህ ቅድመ-ጥንቃቄ የተቀላቀለበት የውሃ አስተዳደር አሰራር ሊከሰት የሚችለውን የኃይል እጥረት ለመቀነስ እና በደረቅ ወራት አስተማማኝ አቅርቦት ለማህበረሰቡ ለማድረስ ያለመ ነው።

ኢትዮጵያ በክረምቱ ወቅት በተልይም በሀምሌ እና ነሀሴ ወራት ያገኘችው የዝናብ መጠን አነስተኛ በመሆኑ ምክንያት ወደ ግድቦች የሚገባው የውሃ መጠን ቀንሷል በዚህም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እቅዱን ለመቀነስ እና የግድቦችን የውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር በጥንቃቂ ለመምራት ተገዷል።

ተቋሙ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፣ ይህ ቅድመ-ጥንቃቄ የተቀላቀለበት የውሃ አስተዳደር አሰራር ሊከሰት የሚችለውን የኃይል እጥረት ለመቀነስ እና በደረቅ ወራት አስተማማኝ አቅርቦት ለማህበረሰቡ ለማድረስ ያለመ ነው። ህዝቡም ይህንን የተፈጥሮ ተፅዕኖ ለማለፍ በቤት እና በስራ ቦታዎች የኃይል ቁጠባ አሰራሮችን እንዲተገብር ጥሪ ቀርቧል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ያጋጠማቸውን የአየር ንብረት ለውጥ እና የዝናብ ማነስ ተፅዕኖ በጋራ እና በሳይንሳዊ መንገድ መወጣት እንደሚገባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ ። እንድ ህዳሴ ያለ የውሃ ግድቦች መገንባታቸው እንደዚህ አይነት ያልተጥበቀ የዝናብ እጥረት በሚያጋጥምበት ወቅት የውሃ ፍሰቱን በማስተካከል የታችኞቹን ሀገራት ከድርቅ ተፅዕኖ ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ይነገራል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow