የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ለምርምርና ለሀገር ዕድገት

የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ቴክኖሎጂ በትምህርት እና በምርምር ዘርፎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

Jun 15, 2026 - 15:58
 0  10
የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ለምርምርና ለሀገር ዕድገት



የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ቴክኖሎጂ በትምህርት እና በምርምር ዘርፎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ አማካሪና ቺፍ ኦፊሰር ዶክተር ሻምበል አስራት እንደገለጹት፣ ቴክኖሎጂው ሁሉንም የስራ ዘርፎች የማገዝ፣ የማሳደግና የአገልግሎት ቅልጥፍናን የመጨመር ትልቅ አቅም አለው።

በተለይም ቀደም ሲል ዓመታትን ይፈጁ የነበሩ የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ለማከናወን እንደሚያግዝ ጠቁመው፣ ተመራማሪዎች በኦንላይን እና በግል ረዳትነት ታግዘው ምርምራቸውን በጥራት እንዲያትሙ የላቀ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል።
ሆኖም የቴክኖሎጂው ጥቅምና ውጤታማነት የሚወሰነው እንደ ግለሰቡ አጠቃቀምና ዕውቀት መሆኑን ባለሙያው አብራርተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው ትልቁ ፈተና የግብረገብነት ወይም የኃላፊነት (Ethical AI) ጉዳይ መሆኑን ያመለከቱት ዶክተር ሻምበል፣ ቴክኖሎጂው በአግባቡና በኃላፊነት ስሜት ካልተያዘ ስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ቀውሶችን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow