የቡናው ዘመን አበቃለት ሊባል ነው ? ወርቅ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አክሊል ተቀዳጀ!

ለዘመናት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ የቆየው ቡና፣ አሁን  በወርቅ ተበልጦ ከዙፋኑ ወርዷል። በ2018 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ብቻ  3.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ

May 6, 2026 - 18:25
 0  2
የቡናው ዘመን አበቃለት ሊባል ነው ? ወርቅ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አክሊል ተቀዳጀ!

የቡናው ዘመን አበቃለት ሊባል ነው ? ወርቅ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አክሊል ተቀዳጀ!

ለዘመናት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ የቆየው ቡና፣ አሁን  በወርቅ ተበልጦ ከዙፋኑ ወርዷል። 2018 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ብቻ  3.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተመዝግቦዋል ዘርፉ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር  አስገራሚ ዕድገት አሳይቶዋል ይህ "ወርቃማው ዘመን" ተብሎ ሊጠራ የሚችለው ክስተት ኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ሲፈታተናት ለነበረው የኢኮኖሚ ቀውስ ወርቅ ተስፋሲሆን፣ ወርቅን የአገሪቱ ቀዳሚ የገቢ ምንጭ በማድረግ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል።

ይህ ስኬት መንግሥት የጥቁር ገበያውን መስኮት በመዝጋትና የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያዎችን በማድረጉ የተገኘ ውጤት ሲሆን በተለይ በባህላዊ ማዕድን አውጪዎች ዘንድ ይባክን የነበረው ሀብት ወደ ብሔራዊ ባንክ ካዝና መፍሰሱ እና አዳዲስ ግዙፍ ማዕድናት መገኘታቸው ለውጡን አፋጥኖታል። አሁን ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳይህ ግዙፍ ገቢ በዜጎች የኑሮ ውድነት ላይ ምን ዓይነት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣል?” የሚለው ሲሆን፣ ወርቅ ኢትዮጵያን ከኢኮኖሚ ማጥ ውስጥ የሚያወጣ አዳኝ ይሆን ወይስ ሌላ የምርት ፖለቲካ? የሚለው የብዙዎች የውይይት መነሻ ሆኗል እርስዎ ምን ይላሉ

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow