የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የነበረውን የንግድ ፈቃድ ሞኖፖሊ አቆመ
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ንግድ ፋይናንስ ቁጥጥርን ለማቃለል እና በባንኮች መካከል የሚታየውን ወጥነት የሌለው የዋጋ አሰጣጥ ለመቅረፍ አዲስ መመሪያ ማሻሻያ ይፋ አድርጓል።
በሀገር ውስጥ የፋይናንስ ዘርፍ ሌላ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ብቻ ለብቻው ይዞት የነበረውን ወደ ቻይና ለሚላኩ የውጭ ምርቶች የኤክስፖርት ፈቃድ የመስጠት መብት (Monopoly) በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ አንስቷል።
- አዲሱ አሰራር፦ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የግል የንግድ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የኤክስፖርት ፈቃድ መስጠት እና ከንግድ ጋር የተያያዙ የባንክ አገልግሎቶችን ማከናወን ይችላል።
- አላማው፦ ማሻሻያው የወጪ ንግድ ሂደትን ለማቀላጠፍ፣ ውድድርን ለመጨመር እና ላኪዎች የመንግስትን ባንክ ብቻ ሳይጠብቁ በግል ባንኮችም ጭምር ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የተደረገ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ መመሪያን አሻሻለ
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ንግድ ፋይናንስ ቁጥጥርን ለማቃለል እና በባንኮች መካከል የሚታየውን ወጥነት የሌለው የዋጋ አሰጣጥ ለመቅረፍ አዲስ መመሪያ ማሻሻያ ይፋ አድርጓል።
What's Your Reaction?