የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማካሄድ ውጤታማ መሆኑን አስታወቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 22ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የገመገመ ሲሆን፣ በዚሁ መድረክ ላይ የተቋሙ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እንደገለጹት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።

ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው እንዳብራሩት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በኢኖቬሽን ዘርፉ 1 ሺህ 714 የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲሁም 25 የጂኦ ስፓሻል ጥናቶች ተካሂደው የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት የተቻለ ሲሆን፣ በተመሳሳይም በሁሉም የስታርትአፕ (የአዳዲስ ስራ ፈጠራ) ንቅናቄዎች አማካኝነት 6 ሺህ 424 አዳዲስ የስራ እድሎችን መፍጠር ተችሏል።
ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የዓለም አንገብጋቢ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ መሆናቸውን የጠቀሱት ዶ/ር በለጠ፣ ዘርፉ የኢትዮጵያን የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲሁም የ2063 የአፍሪካ ህብረት አጀንዳን ለማሳካት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገንዝቦ ሚኒስቴሩ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም የተቋሙን የሰው ሀይል በእውቀትና ክህሎት ለመገንባት የተለያዩ የስልጠና እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መከናወናቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፣ የተቋሙን አሰራሮች በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ ተሰርቶ አመርቂ ውጤቶች መታየታቸውንም ለምክር ቤቱ በሰፊው አስረድተዋል።
What's Your Reaction?