የኬንያ የዋጋ ግሽበት ወደ ገደቡ ሲጠጋ የኢትዮጵያው ቀስ በቀስ እየቀነሰ ነው ተባለ
ኬንያ፦ ግሽበት 7.3% ↑ (በ40 ወራት ከፍተኛው) ኢትዮጵያ፦ ግሽበት 14.9% ↓ (ለሁለተኛ ወር ቀነሰ)ነዳጅ ለሁለቱም የጋራ ስጋት ሆኗል።በተለይ በኢትዮጵያ ያለው ውጥረት ግሽበቱን የመቀነስ ጥረቱን ሊያደናቅፍ ይችላል የሚል ስጋት አለ .
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም.
በምሥራቅ አፍሪካ ትልልቅ ኢኮኖሚዎች መካከል የሚመደቡት ኬንያና ኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ረገድ ተቃራኒ አቅጣጫእየተከተሉ ነው። የኬንያ ግሽበት ዝቅተኛ ቢሆንም እየጨመረ ነው፤ የኢትዮጵያው ደግሞ ከፍተኛ ቢሆንም እየቀነሰነው።
የኬንያ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ (KNBS) ትናንት ጥቅምት 20 ባወጣው መረጃ፣ የአገሪቱ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበትመስከረም ከነበረበት 6.8% በያዝነው ወር ጥቅምት ወደ 7.3% ከፍ ብሏል። ይህ ባለፉት በኬንያ 40 ወራት ውስጥየተመዘገበው ከፍተኛውየዋጋ ግሽበት ነው። ለጭማሪው ዋናው ምክንያት የነዳጅ ዋጋ እንደሆነ ተነግሮዋል ። በአንድወር ውስጥ የቤንዚን ዋጋ በሊትር ከ215 ወደ 228 የኬንያ ሽልንግ (6%)፣ ማለትም ከ266.83 ብር ወደ 288. ብር ከፍ ብሎዋል የናፍታ ዋጋ ከ219 ወደ 229 ሽልንግ (4.4%) ጨምሯል፤ በአኢቶጳ በር ከ 271 ወደ 284 የ 13 ብር ጭማሪ ማለት ነው የኬሮሲን ዋጋ ደግሞ ከ193 ወደ 221 ሽልንግ (14.7%) ዘሏል።
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ወደ ሌሎች ዘርፎችም ተዛምቷል። የትራንስፖርት ወጪ በዓመት 17.1% ጨምሯል፤ የምግብ ዋጋደግሞ 10.2% ጨምሯል። ምግብና ነዳጅን የማይጨምረው ዋናው ግሽበት ከ4.0% ወደ 4.3% ከፍ ብሏል።
ግሽበቱ አሁን የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ ከሚታገሰው የ7.5% ከፍተኛ ገደብ በ0.2 ነጥብ ብቻ ያነሰ ነው። ባንኩ በያዝነው ወር መጀመሪያ የመሠረታዊ ወለድ ምጣኔውን በ8.75% እንዳይለወጥ ያደረገ ሲሆን፣ ተጨማሪ የወለድ ቅነሳ የማድረግዕድሉ እየጠበበ መምጣቱን ተንታኞች ይገልጻሉ።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በአዝነ ወር አጋማሽ ባወጣው መረጃ፣ የመስከረም ወር ዓመታዊግሽበት 14.9% ሆኗል። ይህም በነሀሴ ወር ከነበረው 15.1% በትንሹ ቀንሷል። ግሽበቱ ለተከታታይ ሁለት ወራትቢቀንስም፣ ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር (13.2%) ጋር ሲነጻጸር አሁንም ከፍተኛ ነው። የምግብ ግሽበት 14.8%፣ ከምግብውጭ ያሉ ዕቃዎች ግሽበት ደግሞ 15.1% ሆኗል። የትራንስፖርት ዋጋ 16% ጨምሯል፤ ይህም ከኬንያው ጋር ተቀራራቢነው።
በኢትዮጵያ ግሽበቱ ከብር ዋጋ መዳከም ጋር የተያያዘ ነው። በጥቅምት 19 በተካሄደው የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬጨረታ አንድ ዶላር በአማካይ 159.70 ብር ተሸጧል። ብሔራዊ ባንኩ ግሽበትን ለመቆጣጠር በሰኔ ወር የወለድምጣኔውን ወደ 16% ከፍ ያደረገ ሲሆን፣ ግሽበቱ በሚቀጥሉት ወራትም ከ10% በላይ እንደሚቆይ ይጠብቃል።
በርግጥ የሁለቱ አገሮች የእድገት ገጽታይለያያል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በ2026 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚበ9.2%፣ የኬንያ ደግሞ በ4.5% እንደሚያድግ ተንብዩአል። ይሁን እንጂ ብር በመዳከሙ ምክንያት፣ በዶላር ሲለካ ኬንያአሁንም ኢትዮጵያን በልጣ በቀጣናው ትልቁ ኢኮኖሚ ያልት ሀገር ሆናለች።
የዓለም የነዳጅ ዋጋ መለዋወጥ ለሁለቱም ሀገራት የጋራ ስጋት ሆኖ ቀጥሏል። የኢትዮጵያ የያዝነው ወር የግሽበት መረጃ በመጭው ህዳር ወር አጋማሽ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የቀጠለው ውጊያና ከኤርትራ ጋር ያለው ውጥረት የመንግሥትን ወጪ በመጨመርና የአቅርቦት መስመሮችን በማወክ ግሽበቱን የመቀነስ ጥረቱን ሊያደናቅፍ ይችላል የሚል ስጋት አለ .
ምንጮች፦ KNBS፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት፣ የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ (CBK)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ(NBE)፣ IMF World Economic Outlook (ኦክቶበር 2026)
What's Your Reaction?