የጠፈር ምርምር አደጋ—የጄፍ ቤዞስ ሮኬት ፈነዳ
ቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ “ብሉ ኦሪጂን” ኩባንያ ግዙፍ ሮኬት በፍሎሪዳ የሙከራ ወቅት በከፍተኛ ፍንዳታ ወደመ። የቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ የጠፈር ኩባንያ የሆነው “ብሉ ኦሪጂን” (Blue Origin)፣ ለቀጣዩ ምህ
የቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ “ብሉ ኦሪጂን” ኩባንያ ግዙፍ ሮኬት በፍሎሪዳ የሙከራ ወቅት በከፍተኛ ፍንዳታ ወደመ።
የቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ የጠፈር ኩባንያ የሆነው “ብሉ ኦሪጂን” (Blue Origin)፣ ለቀጣዩ ምህዋር ተልዕኮ ዝግጅት እያደረገ የነበረው ግዙፍ ኒው ግሌን ሮኬት ትላንት ሐሙስ ምሽት በፍሎሪዳ ኬፕ ካናቬራል የጠፈር ጣቢያ በድንገት ፈንድቶ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ታወቀ።
ባለ 29 ፎቅ ቁመት ያለው ይህ ሜጋ ሮኬት፣ ወደ ጠፈር ከመውጣቱ በፊት ሞተሩ መሬት ላይ ታስሮ የሚሞከርበትን የ“ሃት-ፋየር” (Hot-fire test) ሙከራ እያደረገ በነበረበት ወቅት ነው ባልታወቀ የቴክኒክ ብልሽት ወደ ግዙፍ የእሳት ኳስነት የተቀየረው።
የስፔስ ኤክስ (SpaceX) ባለቤትና የቤዞስ ዋነኛ ተፎካካሪ የሆነው ኢሎን ማስክ በበኩሉ አጋርነቱን ለማሳየት በሚመስል መልኩ “በክስተቱ አዝኛለሁ፣ በፍጥነት እንደምታገግሙ ተስፋ አደርጋለሁ፤ የሮኬት ሳይንስ ከባድ ነው” ሲል መልዕክት አስተላልፏል።
ይህ ፍንዳታ በብሉ ኦሪጂን ብቸኛ የሮኬት ማስወንጨፊያ ሜዳ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ጥገናው በርካታ ወራትን ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል።ይህ አደጋ ብሉ ኦሪጂን ከአማዞን ጋር በመሆን የኢሎን ማስክን ‘ስታርሊንክ’ ለመፎካከር ለጀመረው የሳተላይት ኢንተርኔት ዝርጋታ ትልቅ መስተጓጎል ከመሆኑም በላይ፣ ኩባንያው ለናሳ (NASA) የአርጤምስ የጨረቃ ጉዞ ፕሮግራም የሰዎችን ማረፊያ መንኮራኩር ለመስራት ከገባው ውል አንጻር በጠፈር ምርምር ታሪኩ ላይ የገጠመው ታላቅ የቴክኒክ መሰናክል ተደርጎ ተመዝግቧል።
What's Your Reaction?