የ 40 ሚሊዮን ዶላር የ"አረንጓዴ አሻራ" ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጀመረ

May 26, 2026 - 20:24
 0  44
የ 40 ሚሊዮን ዶላር የ"አረንጓዴ አሻራ" ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጀመረ

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር የሚያስችል የ 40 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ፈንድ የተመደበለት አዲስ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በይፋ ተጀምሯል። ፕሮጀክቱ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 6 ዞኖች ላይ ተግባራዊ ይሆናል።ከ 67 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በደን ለመሸፈን እና የአየር ንብረት መዛባት ተጋላጭ የሆኑ ከ 423 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም (UNEP) ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow