የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጥቅላላ ምርጫ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል -በአማራ እና በትግራይ ክልሎች በ 46 ምርጫ ክልሎች ምርጫ አይካሄድም
ቦርዱ የቅድመ ምርጫ ሥራዎችን (በተለይም ከመጋቢት መጀመሪያ ጀምሮ የተካሄደውን የመራጮች ምዝገባ) በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ገልጿል።የተመዘገቡ መራጮች፦ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለምርጫው መመዝገባቸውን ቦርዱ አረጋግጧል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ትናንት እና ዛሬ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና ለጋዜጠኞች በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ ስለ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ዝግጅቶች እና የድምፅ መስጫ ቀን አፈጻጸም ዝርዝር መረጃዎችን ይፋ አድርገዋል።
በአማራ እና በትግራይ ክልሎች በ 46 ምርጫ ክልሎች ምርጫ አይካሄድም
በጸጥታ ችግሮች እና ወቅታዊ አለመረጋጋቶች ምክንያት በአማራ እና በትግራይ ክልሎች በሚገኙ በርካታ የምርጫ ክልሎች ላይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንደማይደረግ ተገልጿል።በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት የመራጮች ምዝገባ እና የዕጩዎች ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማከናወን ባልተቻለባቸው የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫው ተራዝሟል።
ቦርዱ የቅድመ ምርጫ ሥራዎችን (በተለይም ከመጋቢት መጀመሪያ ጀምሮ የተካሄደውን የመራጮች ምዝገባ) በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ገልጿል።የተመዘገቡ መራጮች፦ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለምርጫው መመዝገባቸውን ቦርዱ አረጋግጧል።የምርጫ ጣቢያዎች፦ በመላ ሀገሪቱ በአጠቃላይ 52,029 የምርጫ ጣቢያዎች ተቋቁመው ወደ ሥራ ገብተዋል።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚያስፈልጉ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች (Ballots) እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ተዘጋጅተው በመላ ሀገሪቱ ወደሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰራጭተው መጠናቀቃቸውን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።ምርጫው ቀደም ሲል በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ተገልጿል።ቦርዱ ከፌዴራል እና ከክልል የፀጥታ ተቋማት፣ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመሆን የምርጫውን የፀጥታ ሁኔታ በ"አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ" ደረጃዎች ከፍሎ ጥናት ማድረጉንና ሰላማዊ የድምፅ መስጠት ሂደት እንዲኖር የክትትል ቡድኖችን ማሰማራቱን አስታውቋል።
የተወዳዳሪዎች ብዛትበምርጫው ላይ ለመወዳደር 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 10,934 ዕጩዎችን (ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች) አቅርበዋል። ከእነዚህም በተጨማሪ 73 የግል ዕጩዎች በምርጫው ይሳተፋሉ።የቦርዱ ማጠቃለያ መልዕክት፦ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ግልጽ፣ ተዓማኒ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የጠበቀ ትብብር እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ የውጭ ሀገር ታዛቢዎችና ዲፕሎማቶችም በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጨምር ማብራሪያው መርዳቱን ጠቁመዋል።
What's Your Reaction?