ትኬት ብቻ ይኑርዎት! የትራምፕ አስተዳደር ለዓለም ዋንጫ ታዳሚዎች የቪዛ ማስያዣ ክፍያን ሰረዘ
መልካም ዜና ለዓለም ዋንጫ ታዳሚዎች፦ የትራምፕ አስተዳደር የ15,000 ዶላር የቪዛ ማስያዣን አነሳ! የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለ2026 ዓለም ዋንጫ ትኬት ለገዙ የ50 አገራት ደጋፊዎች ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረውን የ15,000 ዶላር (11,000 ፓውንድ) የቪዛ ማስያዣ (Bond) ግዴታ ማንሳቱን አስታውቋል
መልካም ዜና ለዓለም ዋንጫ ታዳሚዎች፦ የትራምፕ አስተዳደር የ15,000 ዶላር የቪዛ ማስያዣን አነሳ!
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለ2026 ዓለም ዋንጫ ትኬት ለገዙ የ50 አገራት ደጋፊዎች ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረውን የ15,000 ዶላር (11,000 ፓውንድ) የቪዛ ማስያዣ (Bond) ግዴታ ማንሳቱን አስታውቋል። ይህ ውሳኔ በሰኔ 11 የሚጀመረውን እና በአሜሪካ፣ ካናዳ እንዲሁም ሜክሲኮ በጋራ የሚዘጋጀውን የዓለም ዋንጫ ለመታደም ትክክለኛ ትኬት ይዘው ለሚጓዙ ደጋፊዎች ብቻ የሚሰራ ነው።
ከእነዚህ 50 አገራት መካከል ለውድድሩ ማለፋቸውን ያረጋገጡት አልጄሪያ፣ ኬፕ ቨርዴ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሴኔጋል እና ቱንጓ በዚህ ውሳኔ ተጠቃሚ ይሆናሉ።“ትክክለኛ የዓለም ዋንጫ ትኬት ለገዙ ደጋፊዎች የቪዛ ማስያዣውን አንስተናል” ሲሉ የቆንስላ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞራ ናምዳር ለቢቢሲ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።
ቀደም ሲል ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ብቻ ከዚህ ክፍያ ነፃ የነበሩ ቢሆንም፣ ከረቡዕ ጀምሮ ግን ትክክለኛ ትኬት ያላቸው ደጋፊዎችም እንዲካተቱ ተደርጓል።
ባለፈው ነሐሴ ወር የተጀመረው ይህ የቪዛ ማስያዣ (Bond) ግዴታ፣ ዜጎች ቪዛቸው ካለቀ በኋላ በአሜሪካ እንዳይቀሩ ለመቆጣጠር የታለመ ነበር።
ፊፋ (FIFA) በበኩሉ ውሳኔው ውድድሩ ስኬታማ፣ ሪከርድ ሰባሪ እና የማይረሳ እንዲሆን ከኋይት ሀውስ ጋር ያለውን ቀጣይነት ያለው ትብብር የሚያሳይ ነው ብሏል።
#Lomiinews #WorldCup2026 #Trump #USA #FIFA #FootballNews #VisaUpdate
What's Your Reaction?