ወራቤ ሆስፒታል በከፍተኛ ደረጃ የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል

ወራቤ  ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  የቀዶ ህክምና አገልግሎት በስፋት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል። በወራቤ ሆስፒታል  የፕላስቲክ ቀዶ ህክምናን ለማግኘት ከሞያሌ ጀምሮ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ ታካሚዎች መኖራቸውንም በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፕላስቲክ  እና የሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ህክምና ሀኪም ተባባሪ ፕሮፌሰር  ዶክተር ቴዎድሮስ መለሰ  ተናግረዋል።

Jun 3, 2026 - 10:30
 0  9

ከሚሰጡት  አገልግሎቶች መካከል የቃጠሎ፣   የተፈጥሮ ከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ፣ በተፈጥሮ የሚያጋጥም የስትራክቸር  ችግሮች ፣ የቆዳ ካንሰርን ፣በአደጋ  የሚከሰቱ  የአካል ጉዳቶችን  ጨምሮ በርካታ የህክምና አገልግሎቶች ይጠቀሳሉ።

 በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ብቻ በሳምንት ከ15 እስከ 20 ሰዎች ቀዶ ህክምና ያገኛሉ።  በተጨማሪም በርካታ   የቃጠሎ እና የካንሰር ህክምና  ታማሚዎች ደግሞ በተመላላሽ  እና በተኝቶ ማከም አገልግሎቱን እያገኙ መሆኑ ተገልጿል።
 
አክሎም  በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ያሉ  የህክምና ባለሙያዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን እና የግብዓት አቅርቦት እጥረት መኖሩንም  አንስተዋል። በአሁን ሰዓት በወራቤ ሆስፒታል በዘርፉ ሶስት የህክምና ባለሙያዎች መኖራቸው እና አዲስ አበባ ድረስ  በመመላስ አገልግሎቱን እንደሚሰጡ  በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፕላስቲክ  እና የሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ ሃኪም የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር  ዶክተር ቴዎድሮስ መለሰ ጨምረው ተናግረዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow