የBRICS አባል ሀገራት ስብሰባ በኒው ዴልሂ-ሕንድ

በኒው ዴልሂ-ሕንድ ፅናት፣ ፈጠራ፣ ትብብር እና ዘላቂነትን መገንባት ላይ በማተኮር  እየተካሄደ በሚገኘው የBRICS አባል ሀገራት  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ፣ ኢትዮጵያን የወከሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

May 14, 2026 - 13:42
 0  6

ምንም እንኳ የBRICS ዋና ዓላማ ምጣኔ ሀብታዊ ትብብር ቢሆንም፣ የዘንድሮውን ጉባኤ ያስተናገዱት የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሳንከር እንደገለጹት በምዕራብ እስያ የተጫረው ግጭትና በዓለም አቀፍ የባሕር መስመሮች በተለይም በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያለው የትራፊክ እንቅስቃሴ ለዓለም ምጣኔ ሀብት ወሳኝ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተመከረበት ይገኛል።

በዚህ ውይይት ላይ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አሜሪካና እስራኤል በሀገራቸው ላይ የከፈቱትን ጦርነት “ሕገ-ወጥና የጦርነት ናፋቂነት ተግባር” ሲሉ በመኮነን አባል ሀገራቱ ድርጊቱን እንዲያወግዙ የጠየቁ ሲሆን፣ ይህም በስብስቡ ውስጥ ያሉትን እንደ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያሉ ሀገራትን ግንኙነት እንዲሁም እንደ ኢትዮጵያና ግብፅ ባሉ ሀገራት መካከል ያለውን የውኃ አጠቃቀም ውዝግብ ተከትሎ የሚመጡ ፖለቲካዊ ተጽዕኖዎች በምጣኔ ሀብታዊው ስብስብ ላይ ጥቁር ጥላ ማጥላታቸውን ያሳያል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow