የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሳይበር ደህንነት ‘አስተማማኝ ጋሻ’ ውይስ ‘አደገኛ ሰይፍ’?

ፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር ውስጥ የምትገኘው ዓለማችን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሰውን ልጅ የዕለት ተለት ሕይወት ከማቅለል ባለፈ የሳይበር ስጋቶችን መልክና ባህሪ እየቀየረ እንደሚገኝ ተገለጸ።

May 13, 2026 - 10:34
 0  1
የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሳይበር ደህንነት ‘አስተማማኝ ጋሻ’ ውይስ ‘አደገኛ ሰይፍ’?

የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሳይበር ደህንነትአስተማማኝ ጋሻውይስአደገኛ ሰይፍ’?

በፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር ውስጥ የምትገኘው ዓለማችን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሰውን ልጅ የዕለት ተለት ሕይወት ከማቅለል ባለፈ የሳይበር ስጋቶችን መልክና ባህሪ እየቀየረ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ቴክኖሎጂው በሳይበር ደህንነት ረገድ የጥቃት መከላከያ ጋሻ እና ጥቃት መሰንዘሪያ ሰይፍ በመሆን እርስ በርሱ የሚጋጭ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

 የሰው ሰራሽ አስተውሎት መደበኛ የጥበቃ ስርዓቶች ሊያዩዋቸው የማይችሉትን ጥቃቅን ፍንጮችና መረጃዎች በጥልቀት በመተንተን፣ የሳይበር ጥቃቶች ገና ሳይሰነዘሩ አስቀድሞ ለመለየትና ለመከላከል እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመታየት ላይ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ለደህንነት መጠናከር ትልቅ ተስፋ የሆነው ቴክኖሎጂ፣ በሌላ በኩል ጥቃት አድራሾች የጥቃታቸውን ፍጥነት፣ ጥራትና ውስብስብነት ለመጨመር እንደ አደገኛ መሣሪያ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

 የብሪታኒያ የሳይበር ደህንነት ማዕከል በቅርቡ ያወጣው ትንበያ እንደሚያመለክተው፣ እስከ ፈረንጆቹ 2027 ድረስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም የሳይበር ጥቃቶችን መጠንና ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል። ይህም በዲጂታሉ ዓለም የሚደረገውን የደህንነት ጥበቃ እና የስጋት ቁጥጥር ከምንጊዜውም በላይ ውስብስብ እንደሚያደርገው ተተንብዮአል።

 ኢትዮጵያ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂን ተግባራዊ እያደረገች ባለችበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በበጎ ጎኑ መጠቀም ለስትራቴጂው ስኬት ቁልፍ ሚና አለው። ይሁን እንጂ የስኬቱ ዋስትና የሚረጋገጠው በፋይናንስ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና በሌሎች ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመመከት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ተመልክቷል።

 በመሆኑም ተቋማት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ጥቃቶችን ለመመከት፣ ራሱን ቴክኖሎጂውን እንደ መከላከያ መሣሪያ አድርገው ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ይመከራል። የደህንነት ክፍተቶችን አስቀድሞ ማጥናት፣ የተገኙ ክፍተቶችን መዝጋትና ማንኛውንም የቴክኖሎጂ ሥርዓት ሲተገብሩ "ለደህንነት ቅድሚያ የመስጠት"መርህን መከተል ተቋማት ልዩ ትኩረት ሊሰጡት የሚገባ ተግባር መሆኑ ተላክቷል

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow