ታሪክ ራሱን ሊደግም ነው! ኢትዮጵያ እና የ2028 የአፍሪካ ዋንጫ

ዲስ አበባ — የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) በሀገራችን ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄውን ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ማቅረቡን ተከትሎ፣ በመላው ሀገሪቱ የሚገኘው የስፖርት ቤተሰብ በከፍተኛ መነቃቃት ላይ ይገኛል።

May 12, 2026 - 18:30
May 12, 2026 - 18:37
 0  5
ታሪክ ራሱን ሊደግም ነው! ኢትዮጵያ  እና የ2028 የአፍሪካ ዋንጫ

ታሪክ ራሱን ሊደግም ነው! ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ቆርጣ ተነስታለች

አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) በሀገራችን ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄውን ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ማቅረቡን ተከትሎ፣ በመላው ሀገሪቱ የሚገኘው የስፖርት ቤተሰብ በከፍተኛ መነቃቃት ላይ ይገኛል። 

ይህ ታሪካዊ ጥያቄ ኢትዮጵያ ዋንጫውን ካስተናገደች ከ50 ዓመታት በኋላ የሚመጣ ሲሆን፣ ውድድሩ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ለስፖርታዊው ክብር ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ እግር ኳስ መስራች ለሆነችው ሀገራችን የታላቅነት ዳግም ትንሳኤ ማብሰሪያ እንደሚሆን ይጠበቃል።ውድድሩን በብቃት ለማስተናገድ የሚያስችሉ ግዙፍ የግንባታ ስራዎች አሁንም በከፍተኛ ፍጥነት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፦

 የአደይ አበባ ስታዲየም፦ በአዲስ አበባ የሚገኘውና የግንባታው ሂደት በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሰው ይህ ዘመናዊ ስታዲየም፣ የውድድሩ ዋነኛ ማዕከል እና የግርማ ሞገስ መገለጫ እንደሚሆን ይጠበቃል። በባህር ዳር፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ እና በጅማ የሚገኙ ስታዲየሞች የካፍን (CAF) መስፈርት በሚያሟላ መልኩ እንዲደራጁ እና እንዲታደሱ ታላቅ እቅድ ተይዞላቸዋል።

ኢትዮጵያ ይህንን ታላቅ ክብር ለማግኘት ከባድ ፉክክር ይጠብቃታል ። ከሰሜን አፍሪካዋ ሀያል ሞሮኮ እና ከደቡባዊቷ ጥንካሬ ደቡብ አፍሪካ ጋር የምታደርገው ፉክክር ብርቱ እንደሚሆን ቢታመንም፣ ኢትዮጵያ ባላት ታሪካዊ ድርሻ እና አሁን ላይ በጀመረችው የመሰረተ ልማት ዝግጅት አሸናፊ ሆና ብሔራዊ ኩራት እንደምትወጣ ተስፋ ተጥሎባታል።"እ.ኤ.አ በ1962 አዲስ አበባ ላይ የተዘጋጀውን የአፍሪካ ዋንጫ  በሜዳዋ  እና በደጋፊዋ ፊት አኢትዮጵያ እንዳነሳችው ሁሉ፣ በ2028ም የአፍሪካን ዋንጫ ተቀብላ  ታሪክ ለመድገም ዝግጁ ትሆን ? የእርስዎ አስተያየት ምንድነው?ኢትዮጵያ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ ውድድር ለማስተናገድ ያላት ዕድል ምን ያህል ሰፊ ይመስላችኋል? በመሰረተ ልማት በኩልስ ምን መሟላት አለበት ይላሉ? ሐሳብዎን ያካፍሉን።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow